አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን (Abietu Mebareken Barken)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ያቤጽንም ፡ ሰምተሃል ፡ እንደዚህ ፡ ሲለምንህ
ነፍሱን ፡ ባርከህለታል ፡ አገሩንም ፡ አስፍተህ

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን ፡ አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

2. በልጅህ ፡ ስቃይና ፡ በጣር ፡ የተወለድን
እኛም ፡ ፍሬዎች ፡ ነን ፡ አሰባስበህ ፡ ጠብቀን

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን ፡ አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

3. ከፊትህ ፡ አትጣለን ፡ እንማጸንሃለን
በሞገስህ ፡ አስበን ፡ በመድኃኒትህ ፡ ጐብኘን

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን ፡ አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

4. ሰማያቱም ፡ ይከፈት ፡ መንፈስህ ፡ ይፍሰስልን
ሕይወታችን ፡ ትረስርስ ፡ ነፍሳችን ፡ ትጥገብልን

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን ፡ አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

5. ብቻችንን ፡ አንቅር ፡ አብዛን ፡ እየባረክኸን
አበልጽገን ፡ በጸጋህ ፡ አሳድገን ፡ በቃልህ

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን ፡ አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

6. እግዚአብሔርን ፡ በማወቅ ፡ ምድር ፡ እስክትሞላ
ምልጃችን ፡ ይቀጥላል ፡ ጉልበታችን ፡ ሳይላላ