አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ (Abietu Gulbetie Hoy Ewedehalew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

1. በዙሪያዬ ፡ ሆኖ ፡ ጠላት ፡ ሲያውከኝ
ያሸነፈኝ ፡ መስሎት ፡ ስፎክርብኝ
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ጮህኩኝ
ሰማይን ፡ ዝቅ ፡ አርገህ ፡ ከተፍ ፡ አልክልኝ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ
አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

2. እጆቼን ፡ አንስቼ ፡ ተከፋሁ ፡ አልኩኝ
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ተበቀለልኝ
ምድር ፡ ተናወጠች ፡ ቁጣውም ፡ ነደደ
በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ መብረቅ ፡ አወረደ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ
አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

3. እግሮቸም ፡ ቆሙልኝ ፡ አልተንሸራተቱም
ጠላቶቼን ፡ ያዝኩኝ ፡ አላመለጡኝም
በኮረብቶቹም ፡ ላይ ፡ ለሚያቆመኝ ፡ ጌታ
እስኪ ፡ ላመስግነው ፡ ልዘምር ፡ በዕልልታ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ
አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

4. ለሚታመኑበት ፡ እርሱ ፡ ጋሻ ፡ ነው
ክፉዬን ፡ አይወድም ፡ ይነዳል ፡ ቁጣው
በመቅደሱ ፡ ሆኖ ፡ ድምጼን ፡ ይሰማኛል
እግዚአብሔርን ፡ አይቶ ፡ ጠላቴ ፡ ፈርቶኛል

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ
አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)