አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ለዘላለም ፡ አመሰግንሃለሁ (Abietu Amlakie Lezelalem Amesegenehalew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ለዘላለም ፡ አመሰግንሃለሁ
ክብሬ ፡ ትዘምርልህ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፪x)
ክብሬ ፡ ትዘምርልህ
በእግርህ ፡ ሥር ፡ ልስገድልህ

1. ስልጣን ፡ የተሞላህ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
በክብር ፡ የነገሥህ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
አምሳያ ፡ የሌለህ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
አሸናፊ ፡ አምላክ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ (፪x)

አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ለዘላለም ፡ አመሰግንሃለሁ
ክብሬ ፡ ትዘምርልህ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፪x)
ክብሬ ፡ ትዘምርልህ
በእግርህ ፡ ሥር ፡ ልስገድልህ

2. በመንገድህ ፡ ጻድቅ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
በሥራህ ፡ ሁሉ ፡ ቸር ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
በምክርም ፡ ታላቅ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
የልጆች ፡ ክብር ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ (፪x)

አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ለዘላለም ፡ አመሰግንሃለሁ
ክብሬ ፡ ትዘምርልህ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፪x)
ክብሬ ፡ ትዘምርልህ
በእግርህ ፡ ሥር ፡ ልስገድልህ

3. የማታንቀላፋ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
የእስራኤል ፡ ጠባቂ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ሥምህ ፡ የከበረ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሕዝብህ ፡ ተዋጊ ፡ ዘላለም ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ (፪x)