አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ (Abiet Endiet Talaq Neh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በቃ ፡ አልፈልግም ፡ ልቤን ፡ ውሰደው
አዕምሮዬን ፡ ግዛው ፡ ላአንተው ፡ አድርገው
ዝም ፡ ልበልና ፡ ኃይልህን ፡ ልመልከት
ሌላው ፡ ሃሣቤ ፡ ይብቃ ፡ ይከተት

አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ?
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ

ሌት ፡ በመኝታ ፡ እንዳስብህ ፡ አንተን
ቀን ፡ በሥራዬ ፡ እንዳውጠነጥን
ነህና ፡ ለነፍሴ ፡ ዕርካታና ፡ ደስታ
ክብርህን ፡ ላስበው ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ

አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ?
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ
የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ

እጄን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አድርጌ ፡ ተደነቅሁ
ሥራህንም ፡ ሳየው ፡ በደስታ ፡ ተሞላሁ
በዕውነት ፡ ተረዳሁ ፡ የአንተን ፡ ታላቅነት
እንዲሁም ፡ አስተዋልሁ ፡ የእኔን ፡ ውዳቂነት

አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ?
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ
የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ

ለአንተ ፡ ሚገባህ ፡ ክብርን ፡ ለመስጠት
በመንፈስ ፡ ሳስብህ ፡ ያኔ ፡ ተረዳሁት
አሁን ፡ ቃል ፡ ኪዳኔ ፡ የመጨረሻው
ተዋርጄ ፡ እንድኖር ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ ምሻው

አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ?
እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ?
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ
የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ (፪x)

ደረጀ ፡ ከበደ