አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ የሆነው (Abiet Egziabhier Ersu Amlak Yehonew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


አዝ፦ አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ የሆነው
እንዴት ፡ የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ህዝብ ፡ ነው

አላማ ፡ ይዞ ፡ የተሰለፈ
ግርማ ፡ ሞገሱ ፡ አምላኩ ፡ የሆነ
መርዛሙን ፡ እባብ ፡ ረጋግጦት ፡ ያልፋል
የጠላቶቹን ፡ መንደር ፡ ይወርሳል

አዝ፦ አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ የሆነው
እንዴት ፡ የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ህዝብ ፡ ነው

ምድረ ፡ በዳውን ፡ ዓለምልሞለት
ጥቂቱን ፡ ነገር ፡ ጌታ ፡ ባርኮለት
በሰላም ፡ ውሎ ፡ በሰላም ፡ ያድራል
እግዚአብሔር ፡ ህዝቡን ፡ እንዴት ፡ ወዶታል

አዝ፦ አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ የሆነው
እንዴት ፡ የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ህዝብ ፡ ነው

በረሃብ ፡ ዘመን ፡ መናን ፡ አብልቶ
ጭንቀት ፡ ሲበዛ ፡ ሰላምን ፡ ሰጥቶ
ከኋላ ፡ ከፊት ፡ ሆኖ ፡ ከለላ
እርሱ ፡ ይመራዋል ፡ በድል ፡ በተድላ

አዝ፦ አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ የሆነው
እንዴት ፡ የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ህዝብ ፡ ነው

በብርቱ ፡ ታምኖ ፡ ሁሉን ፡ ይረታል
በእርሱ ፡ ተዋግቶ ፡ ምርኮን ፡ ይማርካል
አይናወጥም ፡ ልቡ ፡ ጽኑ ፡ ነው
ጋሻ ፡ መከታው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ የሆነው
እንዴት ፡ የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ህዝብ ፡ ነው