አባትን ፡ ሰብሁ (Abaten Sebehu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አባትን ፡ ሰብሑ ፡ ስለ ፡ ቸርነቱ
በታላቅ ፡ ፍቅሩ ፡ ልጆቹን ፡ ያስባል ፡ ወድሱ
እላንት ፡ የሰማይ ፡ ሰራዊት ፡ የሆዋን ፡ ወድሱ

መድህንን ፡ ሰብሑ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ርሕራሔው
በታላቅ ፡ ጸጋው ፡ ለሕዝቡ ፡ ያስባል
ጐበዞች ፡ ትንሾች ፡ ሽማግሎች ፡ ልጆች ፡ መድህንን ፡ ወድሱ

መንፈስን ፡ ሰብሑ ፡ አጽናኤ ፡ እስራኤል
ከአብና ፡ ከወልድ ፡ ሊባርከን ፡ ተልኮ ፡ ሰብሑ
አብን ፡ ወልድን ፡ መንፈስንም ፡ ስላሴን ፡ ወድሱ