አባታችን ፡ ጌታችን ፡ ሆይ (Abatachen Gietachen Hoy)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አባታችን ፡ ጌታችን ፡ ሆይ !
የምትኖር ፡ በሰማይ
መንግሥትህ ፡ ትምጣልን ፡ ከላይ
ክብርህን ፡ እንድናይ
ክብርህን ፡ እንድናይ

ፈቃድህ ፡ በሰማይ ፡ ቀድም
ሕይወት ፡ እንደሆነች
እንዲሁም ፡ በምድር ፡ ደግሞ
ሰላምህን ፡ ስጠን
ሰላምህን ፡ ስጠን

ስጠነ ፡ ለሕዝብህ ፡ ዛሬ
የዕለት ፡ ሲሳያችን
በደላችንን ፡ ሁሉ
ይቅር ፡ እንድትለን
ይቅር ፡ እንድትለን

ጌታ ፡ ሆይ ፡ አታግባን ፡ አሁን
ከክፉ ፡ ፈተና
አምላክ ፡ አንተ ፡ ካልረዳኸን
ኃይል ፡ የለንምና
ኃይል ፡ የለንምና

ኃይልና ፡ ምሥጋና ፡ ክብርም
መንግሥትም ፡ የአንተ ፡ ናት
አሜን ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም
ይሁንልን ፡ ዕረፍት
ይሁንልን ፡ ዕረፍት