From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አንድ ፡ ቀን ፡ ለዓይናችን ፡ ይወጣል
አንርሳ ፡ እንዲመጣ
ኢየሱስ ፡ ለፍርድ ፡ ይመለሳል
የመላ ፡ ዓለም ፡ ዳኛ
እላንት ፡ ኃጢአን ፡ አስተውሉ
መሸሻ ፡ የለም ፡ ከፊቱ
ዓይኑ ፡ ያያል ፡ በሁሉ
ሲነፋ ፡ የፍርድ ፡ መለከት
ሙታኑ ፡ ይነሣሉ
የምድር ፡ ልጆች ፡ በድንገት
በፊቱ ፡ ሊከማቹ
የሞቱ ፡ በሕይወት ፡ ያሉ
ለአምላክ ፡ ሊቆጣጠሩ
በጽድቅ ፡ ይፈረዳሉ
ከአዳም ፡ ውድቀት ፡ እስካሁኑ
ሰዎች ፡ የሠሩት ፡ ሁሉ
የተጻፈበት ፡ መጽሐፉ
ሊከፍት ፡ በትዕዛዙ
ተመርምሮ ፡ እያንዳንዱ
እንደ ፡ ሥራው ፡ በሕይወቱ
ሊቀበል ፡ ግቡን ፡ ፍርዱ
ከአምላክ ፡ ቃል ፡ የሚዛቡ
ተደልለው ፡ በዓለም
ከንቱነትን ፡ የሚመኙ
ከእርሱ ፡ ሊወርሱ ፡ መርገም
ደሞዝን ፡ በዚህ ፡ ወሰዱ
በጸጸት ፡ ሊፈራገጡ
ከሰይጣን ፡ ከመላዕክቱ
ኦ! ኢየሱስ ፡ የፍርድ ፡ ቀን ፡ ሲሆን
ስለ ፡ ትሩፋትህ ፡ ማረኝ
እንደ ፡ ቸር ፡ አባር ፡ ለእኔ ፡ ሁን
ሰማይን ፡ ክፈትልኝ
በሰይጣን ፡ ላይ ፡ ድል ፡ የነሣህ
ከኃጢአት ፡ እሥር ፡ የፈታህ
ምላልኝ ፡ ያን ፡ ብሩክ ፡ ተስፋህ
ኦ! ጌታዬ ፡ በቶሎ ፡ ና!
መምጣትህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ድካም ፡ ጭንቀት ፡ የሚመላ
ያሁን ፡ ዘመን ፡ ይበራል
ይቀርባል ፡ ዕለት ፡ ዕለት
በአንተ ፡ ረድዔትና ፡ ሥምረት
ያ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብረት
|