From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
"ሰማይ ፡ ምድር ፡ ይስማኝ ፡ ፍጥረት ፡ ያድምጠኝ
እግዚአብሔር ፡ ያሰበው ፡ ጸሎቱ ፡ የተሰማ ፡ ያ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ
እኔ ፡ ነኝ"
በቆዘምኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ
ከፍ ፡ ሊያደርገኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ
መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ
ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ
ባለቀስኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ
ደግሞ ፡ ሊያስቀኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ
መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ
ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ
የካሳ ፡ ዘመን ፡ አለ ፡ ከፊቴ (፪x)
ልውጣ ፡ ልውረሰው ፡ ወግድ ፡ ጠላቴ ፡ ዞርበል ፡ ጠላቴ
የበቀል ፡ ቅባት ፡ ስላረፈብኝ
ኪዳንህ ፡ ፈርሷል ፡ ዳግም ፡ ላትገዛኝ (፪x)
ወራሽ ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ እርስት ፡ እንደሌለው
የሃዘን ፡ የለቅሶ ፡ ቤቴን ፡ ልታደርገው
ወገን ፡ ዘመድ ፡ ያጣ ፡ ባይተዋር ፡ ብቸኛ
ብለህ ፡ ስትጣራ ፡ ጌታ ፡ መጣልኛ
በሰው ፡ አቆጣጠር ፡ ቢመስል ፡ የዘገየ
እውነተኛ ፡ ዳኛ ፡ መገፋቴን ፡ አየ
ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁ
በጨለማ ፡ ብሄድ ፡ ጌታ ፡ ብርሃኔ ፡ ነው
የጠራኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይጥልም ፡ አውቃለሁ
እንዳልሰማ ፡ የአንተን ፡ ስብከት
ውሸታም ፡ ነህ ፡ የውሸት ፡ አባት
ፈጣሪዬን ፡ ለእኔ ፡ ልታማ
ብዙ ፡ ሞከርክ ፡ መች ፡ ልታቅማማ
እኔስ ፡ የማውቀው ፡ ይሄን ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነው (እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም) (፬x)
በቆዘምኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ
ከፍ ፡ ሊያደርገኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ
መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ
ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ
ባለቀስኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ
ደግሞ ፡ ሊያስቀኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ
መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ
ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ
የካሳ ፡ ዘመን ፡ አለ ፡ ከፊቴ (፪x)
ልውጣ ፡ ልውረሰው ፡ ወግድ ፡ ጠላቴ ፡ ዞርበል ፡ ጠላቴ
የበቀል ፡ ቅባት ፡ ስላረፈብኝ
ኪዳንህ ፡ ፈርሷል ፡ ዳግም ፡ ላትገዛኝ (፪x)
ከላይ ፡ አዞልኛል ፡ የሰማይ ፡ አባቴ
ሞልቶ ፡ እንዲትረፈረፍ ፡ በበረከት ፡ ቤቴ
የሚያስፈልገኝን:ስለሚያውቅልኝ
ከእኔ ፡ ይልቅ ፡ ለእኔ ፡ የሚያስብልኝ
አምላክ ፡ አለኝና ፡ እጅግ ፡ ባለጠጋ
ለምንስ ፡ ልሳቀቅ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ልሥጋ
ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁ
በጨለማ ፡ ብሄድ ፡ ጌታ ፡ ብርሃኔ ፡ ነው
የጠራኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይጥልም ፡ አውቃለሁ
እንዳልሰማ ፡ የአንተን ፡ ስብከት
ውሸታም ፡ ነህ ፡ የውሸት ፡ አባት
ፈጣሪዬን ፡ ለእኔ ፡ ልታማ
ብዙ ፡ ሞከርክ ፡ መች ፡ ልታቅማማ
እኔስ ፡ የማውቀው ፡ ይሄን ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነው (እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም) (፬x)
|