ተገልጦልኛል (Tegeltolegnal) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 2.jpg


(2)

የካሳ ፡ ዘመን
(Yekasa Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

አዝእውነት ፡ ተገልጦልኛልና ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (፪x)
በአለማወቅ ፡ የኖርኩባቸው ፡ ዘመናቶቼ
ዳግመኛ ፡ እንዳላያቸው ፡ በአምላኬ ፡ እረሳኋቸው (፪x)

ጸያፍ ፡ ነበረ ፡ ምግባሬ ፡ በደሌም ፡ በዝቶ ፡ ነውሬ
እርሱ ፡ ባይረዳኝ ፡ ረድኤቴ ፡ አክትሞ ፡ ነበር ፡ ሕይወቴ
ከገደል ፡ አፋፍ ፡ መለሰኝ ፡ የሞትን ፡ ጽዋ ፡ ሳልቀምሰው
እራርቶልኛል ፡ በፍቅሩ ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ይድረሰው

ለአምላኬና ፡ ለሥሙ ፡ ክብር
ስዘምር ፡ ውዬ ፡ ስዘምር ፡ ባድር
ለአምላኬማ ፡ አይገልጽልኝም
የውስጥ ፡ የልቤን ፡ ያለኝን ፡ ፍቅር (፪x)

አዝእውነት ፡ ተገልጦልኛልና ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (፪x)
በአለማወቅ ፡ የኖርኩባቸው ፡ ዘመናቶቼ
ዳግመኛ ፡ እንዳላያቸው ፡ በአምላኬ ፡ እረሳኋቸው (፪x)

የጽድቅን ፡ መንገድ ፡ ስልሳውቀው
ጉዙው ፡ አድክሞኝ ፡ ዝያለሁ
እረፍት ፡ የሌለው ፡ እርካታ
ውሸት ፡ ነው ፡ የዓለም ፡ ደስታ
መውጣት ፡ መውረዱ ፡ መልፋቱ
እርባን ፡ አቢስ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ
ዓይኖቹ ፡ በርተው ፡ ላየው ፡ ሰው
የኢየሱስ ፡ መሆን ፡ መታደል ፡ ነው

ለአምላኬና ፡ ለሥሙ ፡ ክብር
ስዘምር ፡ ውዬ ፡ ስዘምር ፡ ባድር
ለአምላኬማ ፡ አይገልጽልኝም
የውስጥ ፡ የልቤን ፡ ያለኝን ፡ ፍቅር (፪x)