ሳስበው (Sasebew) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 2.jpg


(2)

የካሳ ፡ ዘመን
(Yekasa Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

አዝሳስበው (፫x) ፡ የአምላኬን ፡ ምህረት ፡ ቸርነቱን
ዘምር ፡ ያሰኘኛል ፡ እንደገና
በዋዛ ፡ ሚታለፍ ፡ መች ፡ ሆነና (፪x)

አላየውም ፡ እኔስ ፡ እንደዘበት
የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ አይቻለሁ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ቸር ፡ ነህ ፡ ብለው
ፍቅር ፡ ነህ ፡ ብለው ፣ ደግ ፡ ነህ ፡ ብለው
ቃላት ፡ አጥቼ ፡ እንጂ
ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ሲያንስ ፡ ነው (፬x)

ሞገስ ፡ ያገኘሁት ፡ አንተን ፡ አግኝቼ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ
የሰላሜ ፡ ምክንያት ፡ መሆንህን ፡ ታውቀዋለች ፡ ነፍሴ (፬x)

ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ፡ ኦ ፡ ማን ፡ ነበርኩኝ
ታማኝ ፡ አርገህ ፡ ቆጥረኸኝ ፡ በቤትህ ፡ የሾምከኝ
እራሴን ፡ አውቀዋለሁ ፡ ታናሹን ፡ ሰው
እንተው ፡ ነህ ፡ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)

ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ፡ ኦ ፡ ማን ፡ ነበርኩኝ
ታማኝ ፡ አርገህ ፡ ቆጥረኸኝ ፡ በቤትህ ፡ የሾምከኝ
እራሴን ፡ አውቀዋለሁ ፡ ታናሹን ፡ ሰው
እንተው ፡ ነህ ፡ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)

አዝሳስበው (፫x) ፡ የአምላኬን ፡ ምህረት ፡ ቸርነቱን
ዘምር ፡ ያሰኘኛል ፡ እንደገና
በዋዛ ፡ ሚታለፍ ፡ መች ፡ ሆነና

አላየውም ፡ እኔስ ፡ እንደዘበት
የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ አይቻለሁ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ክብሬ ፡ ነህ ፡ ብለው
ሞገሴ ፡ ብለው ፣ ማዕረጌ ፡ ብለው
ቃላት ፡ አጥቼ ፡ እንጂ
ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ሲያንስ ፡ ነው (፬x)

ልቀኝልህ ፡ ቅኔ ፡ ብትወደኝ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ሰው ፡ መሆኔ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲረሳኝ ፡ ያሰብከኝን ፡ አልረሳውም ፡ እኔ
አይተህ ፡ እንዳላየስ ፡ መች ፡ አለፍከኝ ፡ አልረሳውም ፡ እኔ
ከመንገድ ፡ ወድቄ ፡ ራራህልኝ ፡ አልረሳሁም ፡ እኔ
ቁስሌን ፡ ሳትጸየፍ ፡ ያከምክልኝ ፡ አልረሳውም ፡ እኔ

ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ፡ ኦ ፡ ማን ፡ ነበርኩኝ
ታማኝ ፡ አርገህ ፡ ቆጥረኸኝ ፡ በቤትህ ፡ የሾምከኝ
እራሴን ፡ አውቀዋለሁ ፡ ታናሹን ፡ ሰው
እንተው ፡ ነህ ፡ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)

ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ፡ ኦ ፡ ማን ፡ ነበርኩኝ
ታማኝ ፡ አርገህ ፡ ቆጥረኸኝ ፡ በቤትህ ፡ የሾምከኝ
እራሴን ፡ አውቀዋለሁ ፡ ታናሹን ፡ ሰው
እንተው ፡ ነህ ፡ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (፪x)