From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ፈረሱንና ፡ ፈረሰኛውን
በባሕር ፡ የጣለ ፡ እኛን ፡ አሻግሮን
በሚያስፈራ ፡ ግርማው ፡ ከፊት ፡ እየመራ
ነጥቆ ፡ ያስመለጠን ፡ ከዚያ ፡ ባለጋራ (፪x)
አዝ፦ ትላንት ፡ የረዳን ፡ ያገዘን ፡ ጌታ
ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ አለና ፡ እንጨምር ፡ ምሥጋና (፪x)
ብዙ ፡ ብዙ (ምሥጋና)
ከልባችን (ምሥጋና)
እንሰዋ (ምሥጋና)
ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x)
ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ ፡ ቀኑን ፡ በደመና
እስራኤልን ፡ የሚጠብቅ ፡ ለአፍታ ፡ ደክሞ ፡ አያውቅም
መንገድ ፡ አስጀምሮ ፡ ጥሎ ፡ የማይጠፋ
የማይሻር ፡ ኪዳን ፡ አለው ፡ ጽኑ ፡ ፍቅር ፡ ቀን ፡ ቢከፋ
እንደኃያልና ፡ እንደጨካኝ ፡ ወጥቶ
በሰልፉ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ ውጊያውን ፡ ተዋግቶ
ድል ፡ አድርጐ ፡ ባለድል ፡ ያደረገን ፡ እርሱ ፡ ነው
ይክበር ፡ ይንገሥልን ፡ ወደን ፡ እናምልከው ፡ ፈቅደን ፡ እናምልከው
አዝ፦ ትላንት ፡ የረዳን ፡ ያገዘን ፡ ጌታ
ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ አለና ፡ እንጨምር ፡ ምሥጋና (፪x)
ብዙ ፡ ብዙ (ምሥጋና)
ከልባችን (ምሥጋና)
እንሰዋ (ምሥጋና)
ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x)
ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ ፡ ቀኑን ፡ በደመና
እስራኤልን ፡ የሚጠብቅ ፡ ለአፍታ ፡ ደክሞ ፡ አያውቅም
መንገድ ፡ አስጀምሮ ፡ ጥሎ ፡ የማይጠፋ
የማይሻር ፡ ኪዳን ፡ አለው ፡ ጽኑ ፡ ፍቅር ፡ ቀን ፡ ቢከፋ
ብዙ ፡ ብዙ (ምሥጋና)
ከልባችን (ምሥጋና)
እንሰዋ (ምሥጋና)
ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x)
|