From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ማደግ ፡ እሻለሁ ፡ አንተን ፡ መምሰል
ግን ፡ አቅቶኛል ፡ ክብሬን ፡ መጣል
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ ልቤን ፡ አድክሞት
ለአንተ ፡ እንዴት ፡ ልኖር ፡ ለሌላው ፡ ሳልሞት
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ ልቤን ፡ አዝሎት
ለአንተ ፡ እንዴት ፡ ልኖር ፡ ለሌላው ፡ ሳልሞት
አዝ፦ ለውጠኝ (፫x) ፡ ለውጠኝ (፫x)
ቃል ፡ ኪዳኔን ፡ ያጠፍኩኝ
ደካማ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ
እንዲያው ፡ አያለሁ ፡ ልብ ፡ ብዬ
እጮሃለሁ ፡ እንዲህ ፡ ብዬ (፪x)
እጄን ፡ ያዘኝና ፡ አስጠጋኝ
ወደራስህ ፡ ሳበኝ (፪x)
ከካቻምና ፡ የአምና ፡ ከአምናው ፡ የዘንድሮ
ሕይወቴ ፡ ካልታየ ፡ ስምህ ፡ በእኔ ፡ ከብሮ
መኖርስ ፡ ምንድንነው ፡ ዘመን ፡ ማስቆጠሩ
እንዲያው ፡ መመላለስ ፡ ፍሬን ፡ ሳያፈሩ
አዝ፦ ቃል ፡ ኪዳኔን ፡ ያጠፍኩኝ
ደካማ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ
እንዲያው ፡ አያለሁ ፡ ልብ ፡ ብዬ
እጮሃለሁ ፡ እንዲህ ፡ ብዬ (፪x)
እጄን ፡ ያዘኝና ፡ አስጠጋኝ
ወደራስህ ፡ ሳበኝ (፪x)
የእምነት ፡ አባቶቼ ፡ አንተን ፡ አስከብረው
የክብርን ፡ ሞት ፡ አዩ ፡ በእምነታቸው ፡ ጸንተው
ፀጋህን ፡ አልብሰኝ ፡ አልኑር ፡ ተሸንፌ
ከሚጠፋው ፡ ዓለም ፡ ጸጸትን ፡ አትርፌ
አዝ፦ ቃል ፡ ኪዳኔን ፡ ያጠፍኩኝ
ደካማ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ
እንዲያው ፡ አያለሁ ፡ ልብ ፡ ብዬ
እጮሃለሁ ፡ እንዲህ ፡ ብዬ (፪x)
እጄን ፡ ያዘኝና ፡ አስጠጋኝ
ወደራስህ ፡ ሳበኝ (፪x)
|