ልቤን ፡ ፈወሰው (Lebien Fewesew) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 2.jpg


(2)

የካሳ ፡ ዘመን
(Yekasa Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

አዝ፦ ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ የገርማል (፫x)
ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ ይደንቃል (፫x)
ንጹህ ፡ ልብን ፡ ስጠኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ
እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ
ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ
እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ

ደንዳናውን ፡ ልቤን ፡ ስበር
የከፉትን ፡ መውደድ
የጠሉትን ፡ ማፍቀር ፡ ይልመድ
ቂመኛውን ፡ ልቤን ፡ ፈውስ

አሃሃሃ ፡ ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ይርዳኝ ፡ መንፈስህ
አሃሃሃ ፡ እኔነቴ ፡ ጠፍቶ ፡ ይታይ ፡ አንተነትህ (፪x)

አዝ፦ ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ የገርማል (፫x)
ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ ይደንቃል (፫x)
ንጹህ ፡ ልብን ፡ ስጠኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ
እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ
ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ
እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ

ይቅር ፡ ማለት ፡ ሽንፈት ፡ ሆኖ ፡ ለእኔ
የወንድሜ ፡ ጠላት ፡ ነፍሰ ፡ ገዳይ ፡ ሆኜ ፡ አይለቅ ፡ ዘመኔ
ለፍርድ ፡ እንዳልበቃ ፡ ለኩነኔ (፪x)

አሃሃሃ ፡ ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ይርዳኝ ፡ መንፈስህ
አሃሃሃ ፡ እኔነቴ ፡ ጠፍቶ ፡ ይታይ ፡ አንተነትህ (፪x)