From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ የሰው ፡ ምኞቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ሌት ፡ ተቀን ፡ በልቡ ፡ ሚያስበው
ዓይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም
ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም
እኔ ፡ ግን ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጥማቴ
ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጉጉቴ
በዚች ፡ ምድር ፡ ሳለች ፡ ሕይወቴ (፪x)
ከአንተ ፡ ሚያገኘውን ፡ ፈልጐ ፡ የመጣ
ከእጅህ ፡ ተቀብሎ ፡ ዳግመኛ ፡ ላይመጣ
እንደልቡ ፡ መሻት ፡ ሁሉን ፡ ብትሰጠው
አንተ ፡ ከሌለኸው ፡ ምንኛ ፡ ምስኪን ፡ ነው (፪x)
ሰው ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል
ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል
የዚህ ፡ ምድር ፡ ክብር ፡ መች ፡ ከልኩስ ፡ ያልፋል
ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል
አዝ፦ የሰው ፡ ምኞቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ሌት ፡ ተቀን ፡ በልቡ ፡ ሚያስበው
ዓይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም
ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም
እኔ ፡ ግን ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጥማቴ
ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጉጉቴ
በዚች ፡ ምድር ፡ ሳለች ፡ ሕይወቴ (፪x)
እንደሰው ፡ ወግ ፡ ልማድ ፡ ዓመታት ፡ ቆጥሬ
ማለፍ ፡ አልፈልግም ፡ ተራ ፡ ኑሮ ፡ ኖሬ
የተጠራሁለት ፡ የክብር ፡ ጥሪ ፡ ነው
ማቅለል ፡ አልፈልግም ፡ እንደዋዛ ፡ ላየው ፡ እንደቀልድ ፡ ላየው
ሰው ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል
ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል
የዚህ ፡ ምድር ፡ ክብር ፡ መች ፡ ከልኩስ ፡ ያልፋል
ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል
ለፍቶ ፡ ያከማቸው ፡ ጐተራው ፡ ሲሞላ
የማይቆርጠው ፡ ጥሙ ፡ ደግሞ ፡ ሲለው ፡ ሌላ
ሲባክን ፡ ይኖራል ፡ ርጋታን ፡ ፍለጋ
ከእረፍት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ ቀርቦ ፡ ሳይጠጋ
|