From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ይሳነዋል
እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ያቅተዋል
የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ታድሶ
እምባችን ፡ ከዓይናችን ፡ ታብሶ (፪x)
እናያለን ፡ እናያለን ፡ እናያለን
በነቢያቱ ፡ አፍ ፡ የተነገረው
የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን (፪x)
በእግዚአብሔር ፡ ሰዎች ፡ የተባለውን
የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን
የወደቀችውን ፡ የዳዊትን ፡ ድንኳን ፡ አነሳለሁ ፡ ያለ
ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ይችላል ፡ ንጉሡ
የቀድሞውን ፡ ግብር ፡ በእጥፍ ፡ እንዲመልስ ፡ በእራሱ ፡ የማለ
ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ይችላል ፡ ንጉሡ (፪x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱ (ይችላል ፡ ንጉሡ) (፬x)
ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x)
የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መሰዊያው ፡ ፈረሰ
ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x)
የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መርገጫው ፡ ፈረሰ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ይሳነዋል
እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ያቅተዋል
የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ታድሶ
እምባችን ፡ ከዓይናችን ፡ ታብሶ (፪x)
እናያለን ፡ እናያለን ፡ እናያለን
በነቢያቱ ፡ አፍ ፡ የተነገረው
የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን (፪x)
በእግዚአብሔር ፡ ሰዎች ፡ የተባለውን
የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን
የገሃነም ፡ ደጆች ፡ የማይቋቋሟት ፡ ታላቅ ፡ የቀደሳት/የመረጣት
ንጉሧ ፡ ነግሶ ፡ ሲገለጥባት
ዝናዋ ፡ ሞገሷ ፡ ከዳር ፡ ዳር ፡ ሲወጣ ፡ ስትሆን ፡ ገናና
ይህን ፡ በዓይናችን ፡ እናያለን ፡ ገና (፪x)
ዝማሬ ፡ ገኖ (እናያለን ፡ ገና)
ምድርን ፡ ሲሞላ (እናያለን ፡ ገና)
ተስፋን ፡ የሰጠው (እናያለን ፡ ገና)
ታማኝ ፡ ነውና (እናያለን ፡ ገና)
ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x)
የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መሰዊያው ፡ ፈረሰ
ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x)
የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መርገጫው ፡ ፈረሰ
ገና ፡ ገና ፡ እናያለን ፡ ገና...
|