ድኛለሁ (Degnalehu) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 2.jpg


(2)

የካሳ ፡ ዘመን
(Yekasa Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

አንዴ ፡ ድኛለሁ ፡ ጽድቅን ፡ ጸድቄ
በከበረው ፡ ደም ፡ ከአብ ፡ ታርቄ
የቃልኪዳን ፡ ልጁ ፡ አድርጐኛል
ከእርሱ ፡ ፍቅር ፡ ማን ፡ ይለየኛል (፪x)

አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ

በአንዱ ፡ አዳም ፡ ምክንያት ፡ ሞት ፡ ወደእኛ ፡ መጣ
አልታዘዝ ፡ ብሎ ፡ ከገነት ፡ ሊወጣ
አምላክ ፡ ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ ወደምድር ፡ ወረደ
ራሱን ፡ ቤዛ ፡ አድርጐ ፡ ሊያጸድቀን ፡ ወደደ

አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ
እግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ
አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ
ሎሌ ፡ ሳልሆን ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ

ዘምሬ ፡ አልጠግብም ፡ ስለመዳኔ
ሌላው ፡ ሌላውማ ፡ ትርፍ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)

አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ

አንዴ ፡ ድኛለሁ ፡ ጽድቅን ፡ ጸድቄ
በከበረው ፡ ደም ፡ ከአብ ፡ ታርቄ
የቃልኪዳን ፡ ልጁ ፡ አድርጐኛል
ከእርሱ ፡ ፍቅር ፡ ማን ፡ ይለየኛል (፪x)

አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ

በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ሳልደክም ፡ ሳልለፋ
ዘለዓለሜ ፡ አማረልኝ ፡ አምላክ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ
እውነትም ፡ መንገድም ፡ ሕይወትም ፡ እርሱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ብዬ ፡ እመሰክራለሁ

አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ
እግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ
አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ
ሎሌ ፡ ሳልሆን ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ

ዘምሬ ፡ አልጠግብም ፡ ስለመዳኔ
ሌላው ፡ ሌላውማ ፡ ትርፍ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)

አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት
(ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ
(ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ
(ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው
(ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ
(ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ