ብርሃን ፡ በራ (Berhan Bera) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 2.jpg


(2)

የካሳ ፡ ዘመን
(Yekasa Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

አዝ፦ በጨለማ ፡ ለነበርነው ፡ ብርሃን ፡ በራ
አሄ ፡ ብርሃን ፡ በራ ፤ እኸ ፡ ብርሃን ፡ በራ
አማኑኤል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ሲሆን ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፤ እኸ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ

በነጻነት ፡ ልንኖር ፡ ነጻ ፡ አወጣን ፡ ጌታ
ዳግመኛ ፡ አንገኝም ፡ በጨለማው ፡ ቦታ
መድሃኒያለም ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
አነጋልን ፡ ድቅድቁን ፡ ሌሊት

መድሃኒያለም ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
አነጋልን ፡ ድቅድቁን ፡ ሌሊት (፪x)
ፍቅር ፡ ነው (፫x)

ጠላቶች ፡ ነበርን ፡ ወዳጅ ፡ አደረገን
ወደ ፡ እራሱ ፡ ጉያ ፡ በፍቅር ፡ አስጠጋን
ከሲኦል ፡ ታደገን ፡ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ ነጠቀን
ለዘለዓለም ፡ እረፍት ፡ ወደ ፡ ቤቱ ፡ አስገባን (፪x)

ፍቅር ፡ ነው ፡ ፍቅር (፫x)
ፍቅር ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅር

አዝ፦ በጨለማ ፡ ለነበርነው ፡ ብርሃን ፡ በራ
አሄ ፡ ብርሃን ፡ በራ ፤ እኸ ፡ ብርሃን ፡ በራ
አማኑኤል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ሲሆን ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፤ እኸ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ

በነጻነት ፡ ልንኖር ፡ ነጻ ፡ አወጣን ፡ ጌታ
ዳግመኛ ፡ አንገኝም ፡ በጨለማው ፡ ቦታ
መድሃኒያለም ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
አነጋልን ፡ ድቅድቁን ፡ ሌሊት

መድሃኒያለም ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
አነጋልን ፡ ድቅድቁን ፡ ሌሊት (፪x)
ፍቅር ፡ ነው (፫x)

በጫንቃችን ፡ ከብዶ ፡ ያጐበጠን ፡ ቀንበር
አንገት ፡ አስደፍቶን ፡ ባሪያ ፡ አድርጐን ፡ ነበር
የማይረሳው ፡ ጌታ ፡ ቀን ፡ ጠብቆ ፡ መጣ
ከኃጢአት ፡ እስራት ፡ እኛን ፡ ሊያወጣ (፪x)

ፍቅር ፡ ነው ፡ ፍቅር (፫x)
ፍቅር ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅር

አዝ፦ በጨለማ ፡ ለነበርነው ፡ ብርሃን ፡ በራ
አሄ ፡ ብርሃን ፡ በራ ፤ እኸ ፡ ብርሃን ፡ በራ
አማኑኤል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ሲሆን ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፤ እኸ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ

በነጻነት ፡ ልንኖር ፡ ነጻ ፡ አወጣን ፡ ጌታ
ዳግመኛ ፡ አንገኝም ፡ በጨለማው ፡ ቦታ
መድሃኒያለም ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
አነጋልን ፡ ድቅድቁን ፡ ሌሊት

መድሃኒያለም ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
አነጋልን ፡ ድቅድቁን ፡ ሌሊት (፪x)
ፍቅር ፡ ነው (፫x)