በድካሜ (Bedekamie) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 2.jpg


(2)

የካሳ ፡ ዘመን
(Yekasa Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ተገልጦ ፡ ስትሰራ ፡ አይቻለሁ
ከእኔ ፡ ምለው ፡ የለም ፡ የሆነው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነው
ላከብርህ ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ ቸሩ ፡ አባቴ
ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ ተንበርክኬ ፡ በጉልበቴ
ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ላክብርህ
ታይብኝ ፡ ከፍ ፡ ብለህ (፪x)

እንደልጅ ፡ አይተኸኝ ፡ በልጅነት ፡ ወራት
ክፉ ፡ አመሌን ፡ ቻልከው ፡ የምህረትህ ፡ ብዛት
አልጨከንክብኝም ፡ እንድሰጥ ፡ ታልፌ
ስንቶችን ፡ ከመንገድ ፡ ካስቀረው ፡ ተርፌ
አለሁ ፡ በገናዬን ፡ ዛሬም ፡ አልሰቀልኩም
ስለቸርነትህ/ስለደግነትህ ፡ መዘመር ፡ አልተውኩን (፪x)

አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ጌታ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና
አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና (፪x)

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ተገልጦ ፡ ስትሰራ ፡ አይቻለሁ
ከእኔ ፡ ምለው ፡ የለም ፡ የሆነው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነው
ላከብርህ ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ ቸሩ ፡ አባቴ
ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ ተንበርክኬ ፡ በጉልበቴ
ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ላክብርህ
ታይብኝ ፡ ከፍ ፡ ብለህ (፪x)

በውድቀቴ ፡ ስቀህ ፡ ጀርባ ፡ አልሰጠኸኝም
ዓይንህም ፡ እንዳየች ፡ አልበየንክብኝም
ይልቅ ፡ አስጠጋኸኝ ፡ መከርከኝ ፡ ለልቤ
ከቶ ፡ እንደማይበጅ ፡ ሰውኛው ፡ ሃሳቤ

ለተፍገመገመው ፡ ኃይልን ፡ የሰጠኸው
የሳተውን ፡ ደግሞ ፡ ቀርበህ ፡ የመለስከው
የእንደገና ፡ አምላክ ፡ አደረከኝ ፡ ቀና
ሃፍረቴን ፡ ሸፍነህ ፡ የቤቴን ፡ ገበና

አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ጌታ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና
አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና (፪x)