ነኛ (Negna) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 3.jpg


(3)


(፫)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

ተናገረኝ እኔም ሰማሁ አምኛለሁ ተቀብዬ
እግዚአብሄር ያለው ይሆናል ሌላውን አልሰማም ብዬ2

ሰው እንደሚለኝ አይደለሁም ሁኔታ እንደሚለኝ ኧረ አይደለሁም
ቃሉ እንደሚለኝ ነኛ ጌታ እንደሚለኝ ነኛ ሰማይ ነው የኔ መገኛ

ልቤ እኮ ያውቀዋል ያውቀዋል
ውስጤም ተረድቶታል ተረድቶታል
ሌላ ሌላ ሰፊ ክብር ሌላ ሌላ ትልቅ ከፍታ
ሌላ ሌላ ያዘጋጀልኝ ሌላ ሌላ አለኮ ጌታ

በእኔ ሊሰራ የወደደውን ስላወቅሁኝ3
ለፈቃዱ ለሃሳቡ እጅ ሰጠሁኝ3
እኔማ የራሴ አይደለሁም ተገዝቻለሁ2
በኢየሱስ ደም ተዋጅቻለሁ2 ለዘላለም

ተናገረኝ እኔም ሰማሁ አምኛለሁ ተቀብዬ
እግዚአብሄር ያለው ይሆናል ሌላውን አልሰማም ብዬ2

ሰው እንደሚለኝ አይደለሁም ሁኔታ እንደሚለኝ ኧረ አይደለሁም
ቃሉ እንደሚለኝ ነኛ ጌታ እንደሚለኝ ነኛ ሰማይ ነው የኔ መገኛ

በሰነፍ ቃል እኔ ሳላቅማማ ያላዋቂ ወሬም ሳልሰማ
ገና ገና እንደ እግዚአብሄር ቃል ገና ገና ይሆንልኛል
ገና ገና መቶ እጥፍ ያንተ ይሁን ብሎ ተናግሮብኛል
አሜን አሜን