ከሰማይ (Kesemay) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 3.jpg


(3)


(Wa)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

ሌላ ፡ አላይም ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ገብቶኛል
ፍቅሩ ፡ እንደ ፡ መልዕቅ ፡ ላይለቀኝ ፡ ይዞኛል
ልቤ ፡ እርፍ ፡ አለ ፡ በቃ ፡ ተረጋጋ
ስሖን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር

ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ምን ፡ ተሽሎኝ ፡ እመርጣለሁ
የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለ ፡ አንተጋ
ወዶ ፡ ፈቅዶ ፡ ለተጠጋ
ቃልህ ፡ የገባው ፡ የተረዳው
የኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ልቡን ፡ የነካው

ከሰማያት ፡ የሆነ ፡ ሰላም ፡ ከሰማይ ፡ የሆነ ፡ ደስታ
በልቤ ፡ ፈሶ ፡ አረስርሶኛል ፡ ሁለንተናዬን ፡ ተቆጣጥሮኛል

ሌላ ፡ አላይም ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ገብቶኛል
ፍቅሩ ፡ እንደ ፡ መልዕቅ ፡ ላይለቀኝ ፡ ይዞኛል
ልቤ ፡ እርፍ ፡ አለ ፡ በቃ ፡ ተረጋጋ
ስሖን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር

ዓሣ ወጥቶ ፡ ከውኃ ፡ ውስጥ
እንደማይኖር ፡ ስፍራ ፡ ቢለውጥ
እኔም ፡ መኖር ፡ የምችለው
ባለህበት ፡ ስገኝ ፡ ነው

መገኛዬ ፡ ነህ ፡ ደህኔነቴ
የሕይወቴ ፡ ዋልታ ፡ መሠረቴ

ከሰማያት ፡ የሆነ ፡ ሰላም ፡ ከሰማይ ፡ የሆነ ፡ ደስታ
በልቤ ፡ ፈሶ ፡ አረስርሶኛል ፡ ሁለንተናዬን ፡ ተቆጣጥሮኛል
ከሰማይ