ኤልሻዳይ (Elshaday) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 3.jpg


(3)


(Wa)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:52
ጸሐፊ (Writer): ታምራት ክፍሌ
(Tamrat Kifle
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

መክፈት፡አይችልም፡ቁልፉ፡በእጁ፡አይደለም፡ወይ፡(፪×)
 ኸረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡
ማክበር፡አችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አደለም፡ሆይ፡
ኸረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡
ማገዝ፡አችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አደለም፡ሆይ
ኸረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡
ይችላል፡ያደርጋል፡ተወራርጃለሁ፡ ነገሬን፡ሰርቶልኝ፡እኔማ፡አቻለሁ፡
ይኸዉ፡ተገርሜ፡እዘምራለሁ፡ ይኸዉ፡ተደንቄ፡እዘምራለሁ፡

1በነቢያት፡መንፈስ፡እኔ፡እገራለሁ፡ በሞተዉ፡ነገር፡ላይ፡
ትንሳዔ፡አወራሁ፡ የደረቁ፡አጥንቶች፡የተበታተኑ፡
ትንቢቱ፡ሲመጣ፡ሰራዊቶች፡ሆኑ፡
ዛሬም፡ይሰራል፡ይሰራል፡ቃሉ፡ይፈጥራል፡ይፈጥራል፡የሌለነ፡ነገር፡ያመጣል፡(፪×)
ዕድሜ፡ቀጥሎ፡ኑር፡አለኝና፡ዘማሬ፡ሰቶ፡ሞላኝ፡ምስጋና፡ ዕልልታ፡ሆኗል፡
መታወቂያዬ፡ሞልቶ፡ይፈሳል፡ሐሴት፡ደስታዬ፡
ምድረበዳዉን፡ኤደን፡በረሐዉ፡ንገነት፡አደረገዉ፡አሀ፡ቀያየረና፡አሀ፡አደረገዉ፡
ከዓለቱ፡ላይ፡ምንጭን፡አፍልቆ፡አጠጣዉ፡ለተጠማዉ፡አሀ፡ተአምር፡ሰራና፡አሀ፡ለተጠማዉ

ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከሁኔታዎች፡በላይ፡
ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከኃያላኖች፡በላይ፡
 ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ………………….

መክፈት፡አይችልም፡ቁልፉ፡በእጁ፡አይደለም፡ወይ፡(፪×)
 ኸረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡
ማክበር፡አችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አደለም፡ሆይ፡
ኸረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡
ማገዝ፡አችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አደለም፡ሆይ
ኸረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡
ይችላል፡ያደርጋል፡ተወራርጃለሁ፡ ነገሬን፡ሰርቶልኝ፡እኔማ፡አቻለሁ፡
ይኸዉ፡ተገርሜ፡እዘምራለሁ፡ ይኸዉ፡ተደንቄ፡እዘምራለሁ፡

2፡-አላሳልፍ፡ያለኝ፡የብረቱ፡መዘጊያ፡አዉቆ፡ተከፈተ፡
 ሆነልኝ፡ማለፊያ፡እግ/ር፡መንገዴን፡ቀና፡ካደረገዉ
 ከፍ፡ከፍ፡እንዳልል፡ከልካይ፡ማነዉ፡
ሂድ፡ተከናወን፡ብሎኛል፡ዉጣና፡ዉረስ፡ብሎኛል፡አዝማቼ፡ከፊቴ፡ቀድሟል፡፪×
ሕልም፡ብዬ፡የነገርኳቸዉ፡የማይፈፀም፡ቅዠት፡መስሏቸዉ፡
ያንን፡ሕልመኛ፡እንየዉ፡ሲሉ፡ጌታም፡ታማኝ፡ነዉ፡መጣ፡እንደ፡ቃሉ፡
ወደ፡ሹመት፡ስፍራ፡መፃተኛዉን፡ሰዉ፡አፈጠነዉ፡አሀ፡አሰቸኮለና፡አሀ፡አፈጠነዉ፡
ወገን፡በሌለበት፡በባእድ፡ምድር፡ላያ፡አነገሰዉ፡ሸላለመና፡አነገሰዉ፡

ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከሹማምንቶች፡በላይ፡
ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከመኳንችች፡በላይ፡
ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ………………….