From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ (Teodros Tadesse)
|
|
፫ (3)
|
አልበም (wa)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ (2018)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፪ (12)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:47
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች (Albums by Teodros Tadesse)
|
|
ምን ጊዜም ማይረሳው ልቤ
ለእኔ ያረገው ውዴ
ብዘምረው ብዘምረው
ውለታው ብዙ ነው ( 2x)
ተስፋ ቢስ ነበርኩ እኔማ ሞቴን የናፈኩኝ
ጨለማ ወርሶት ሕይወቴን መኖር የታከተኝ
አትሞትም በሕይወት ኑር አለኝ ከሰማይ ድምጽ መጣ
ድቅድቁ ሌሊት ነጋልኝ ለእኔም ፀሐይ ወጣ
ተዘርዝሮ አያልቅም ኢየሱስ ችርነቱ
ከአይምሮ በላይ ነው በዝቷል ደግነቱ
ቢወራ ቢነገር የማይሰለቸኝ
የእርሱ ምሕረት ነው ደግፎ ያቆመኝ
እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል
ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል
እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል
ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል
ምን ጊዜም ማይረሳው ልቤ
ለእኔ ያረገው ውዴ
ብዘምረው ብዘምረው
ውለታው ብዙ ነው ( 2x)
በሰው ዓይን የማይሞላውን ሞገስን ያጠገበው
ከተዋረደ ስፍራ ላይ ከትቢያ ላይ ያነሳው
አይገርምም ቢያገለግለው ቢልለት ጐንበስ ቀና
ምሕረቱ የገነነለት ምስክር ነውና
ተዘርዝሮ አያልቅም ኢየሱስ ችርነቱ
ከአይምሮ በላይ ነው በዝቷል ደግነቱ
ቢወራ ቢነገር የማይሰለቸኝ
የእርሱ ምሕረት ነው ደግፎ ያቆመኝ
እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል
ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል
እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል
ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል
|