አመልክሃለሁ (Amelkihalew) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 3.jpg


(3)


(Wa)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

ምን ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁኝ
ምን ፡ እላለሁኝ ፡ መነ ፡ እላለሁኝ
ስትረዳኝ ፡ እያየሁ ፡ ስታግዘኝ ፡ ስታግዘኝ ፡ ስታግዘኝ
የቱን ፡ ዘምሬ ፡ የቱን ፡ እተዋለሁ
ለኔ ፡ ያረክልኝ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ለኔ ፡ ያረክልኝ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው

መልካም ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ መልካምነትስ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል
ፍቅር ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ የፍቅር ፡ ልኩ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል
ኧረ ፡ ማን ፡ ልበልህ ፡ ማን ፡ ልበልህ ፡
ቃል ፡ አጣሁልህ

ከተጣልኩበት ፡ አዘቅት ፡ መጥተህ
ከጠላቴ ፡ እጅ ፡ እኔን ፡ ተናጥቀህ
በደምህ ፡ ገዝተህ ፡ የአንተ ፡ ካረከኝ
እነዴት ፡ አልዘምር ፡ እንዴት ፡ አልቀኝ
ዛሬማ ፡ በላይ ፡ ሆኖአል ፡ ስፍራዬ ፡
በአብ ፡ ቀኝ ፡ ሆኖአል ፡ መቀመጫዬ
ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ይድረስህ
እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ ልዘምርልህ

እንዴት ፡ ላመስግንህ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ላወድስህ
ከቃላት ፡ በላይ ፡ ነፍሴን ፡ አፍስሼ
ሁለንተናዬን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ
በፍቅርህ ፡ ጉልበት ፡ ተረትቻለሁ
ይኽው ፡ ላመልክህ ፡ መጥቻለሁ

መልካም ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ መልካምነትስ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል
ፍቅር ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ የፍቅር ፡ ልኩ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል
ኧረ ፡ ማን ፡ ልበልህ ፡ ማን ፡ ልበልህ
ቃል ፡ አጣሁልህ

ሙት ፡ የነበርኩኝ ፡ በበደል ፡ ብዛት
ሕያው ፡ አረከኝ ፡ ነፍሴን ፡ ቀደስካት
ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኽኝ
በትልቅ ፡ ፍቅርህ ፡ እንዲያው ፡ ወደድከኝ
ጽድቄ ፡ ነህና ፡ ቅድስናዬ ፡
እንከን ፡ የሌለህ ፡ ንጽህናዬ ፡
ብቃት ፡ የለኝም ፡ የምለው ፡ የእኔ
ቤዛ ፡ ባትሆነኝ ፡ አንተ ፡ መድኅኔ

እንዴት ፡ ላመስግንህ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ላወድስህ
ከቃላት ፡ በላይ ፡ ነፍሴን ፡ አፍስሼ
ሁለንተናዬን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ
በፍቅርህ ፡ ጉልበት ፡ ተረትቻለሁ
ይኽው ፡ ላመልክህ ፡ መጥቻለሁ

አመልክሃልሁ
ዘላለሜ ፡ ኢየሱሴ ፡ የእንተ ፡ ነው
አመልክሃለው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ዘመኔን ፡ ውረሰው
ዘመኔ ፡ የአንተ ፡ ነው
ኑሮዬ ፡ የአንተ ፡ ነው