አልባስጥሮስ (Albastros) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 3.jpg


(3)


(Wa)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

መንገዴን ፡ አደራ ፡ ብዬ ፡ ሰጠሁት ፡ ለመድኃኒቴ
ከሁሉ ፡ አስቀድሜ ፡ ከወዳጅ ፡ ዘመድ ፡ ከእናት ፡ ከአባቴ
ዛሬን ፡ አየሁኝ ፡ በደግነቱ ፡ በምሕረቱ
አቀዳጀልኝ ፡ ዓመታቶቸን ፡ በቸርነቱ

ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ዘመን ፡ ከመጣልኝ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ተራው ፡ ከደረሰኝ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
አዳኜ ፡ ኢየሱስን ፡ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ክብር ፡ የሆነልኝ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ማንንም ፡ ዓይንቅም
ደካማን ፡ በመጣል ፡ እርሱ ፡ አይታወቅም
ሰው ፡ የረሳውን ፡ ያስባል ፡ የተጣለውን ፡ ያነሳል
ማን ፡ ወድቆ ፡ ቀረ ፡ ተጥሎ ፡ ደጅ ፡ ተጥሎ ፡ ደጅ
ማን ፡ ወድቆ ፡ ቀረ ፡ ተጥሎ ፡ ደጅ ፡ ተጥሎ ፡ ደጅ

መንገዴን ፡ አደራ ፡ ብዬ ፡ ሰጠሁት ፡ ለመድኃኒቴ
ከሁሉ ፡ አስቀድሜ ፡ ከወዳጅ ፡ ዘመድ ፡ ከእናት ፡ ከአባቴ
ዛሬን ፡ አየሁኝ ፡ በደግነቱ ፡ በምሕረቱ
አቀዳጀልኝ ፡ ዓመታቶቸን ፡ በቸርነቱ

ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ዘመን ፡ ከመጣልኝ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ተራው ፡ ከደረሰኝ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
አዳኜ ፡ ኢየሱስን ፡ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው
ክብር ፡ የሆነልኝ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ላክብረው

ክረምት ፡ ሆነ ፡ በጋ ፡ አይቀያየርም
ቀን ፡ የጐደለለትን ፡ ጀርባውን ፡ አሰጥም
አቅም ፡ ለሌለው ፡ ወገን ፡ አለኝታ
ለደከመው ፡ ሰው ፡ ብርታት ፡ መከታ
እውነትም ፡ አባት ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ
እውነትም ፡ አባት ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ

ትዝ ፡ ሲለኝ ፡ ውለታው
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ያረገው
አይሆንልኝ ፡ ዝም ፡ ማለት
ታሪኬ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ የሆንኩበት
አልባስጥሮሴን ፡ ልስበረው
ውዴ ፡ ኢየሱስን ፡ ላክብረው
የእኔ ፡ ክብር ፡ የእኔ ፡ ደስታ
ሲከብርልኝ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ጌታ
አልባስጥሮሴን ፡ ልስበረው
ውዴ ፡ ኢየሱስን ፡ ላክብረው
የእኔ ፡ ክብር ፡ የእኔ ፡ ደስታ
ሲከብርልኝ ፡ ነው ፡ ይህ፡ ጌታ