ወዳጄ ፡ ኢየሱስ (Wedajie Eyesus) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 1.jpeg


(1)

አያምረኝም
(Ayamregnm)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

 
በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ሞገስ ፡ እየሆንከኝ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በድል ፡ አሻገርከኝ
አሃሃሃሃ ፡ በድል ፡ አሻገርከኝ

እጄን ፡ በጅህ ፡ ይዘህ ፡ እያበረታኸኝ
ያንን ፡ ድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ በድንቅ ፡ አሳለፍከኝ
አሃሃሃሃ ፡ በድንቅ ፡ አሳለፍከኝ

አዝ፦ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
አያልቅም ፡ ውለታህ ፡ ባወራው ፡ ብተርከው (፬x)

ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ ከሆነ ፡ መሥጋና (፪x)
ለስጦታህ ፡ ምላሽ ፡ ከሆነ ፡ ምሥጋና (፪x)
ልዘምር ፡ እንደገና ፤ ላምልክህ ፡ እንደገና (፬x)

አባት ፡ ሆነህ ፡ አሳድገኸኛል
ከእናት ፡ በላይ ፡ ራርተህልኛል
የቅርቤ ፡ ነህ ፡ ውዴ ፡ ለእኔ
መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ በዘመኔ
(፪x)

አዝ፦ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
አያልቅም ፡ ውለታህ ፡ ባወራው ፡ ብተርከው (፬x)

ወግ ፡ ማዕረጌ ፡ ክብሬ ፡ ልበልህ
ውዴ ፡ ብዬ ፡ ስላልጠገብሁህ
የልቤን ፡ የውስጤን ፡ ባይገልጸውም
እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ልበለዉ
የፍቅርህን ፡ ልኩን ፡ ባልገልጸዉ
እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ልበለዉ