መንፈስህን (Menfesehen) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 1.jpeg


(1)

አያምረኝም
(Ayamregnm)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

 
አዝ፦ መንፈስህን ፡ አትውሰድብኝ
አብሮነትህ ፡ ከእኔ ፡ አይለይ ፡ እኔ???
መገኘትህ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ሰላሜ
ሃብቴ ፡ ቅርሴ ፡ እስከዘለዓለሜ

ፈቃድህን ፡ ሃሳብህን ፡ ትቼ
ስቅበዘበዝ ፡ ከቤትህ ፡ ጠፍቼ
ፈቃድህን ፡ መንገድህን ፡ ትቼ
ስቅበዘበዝ ፡ ከቤትህ ፡ ጠፍቼ

ክብር ፡ ጠፍቶ ፡ ቅጥር ፡ ፈርሶ
ጠላት ፡ ገባ ፡ ወደቤቴ
ሰላም ፡ ቀርቶ ፡ ለቅሶ ፡ ሞልቶት
ዐይኔን ፡ በዕምባ

እንዳልሸሽህ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ
የልጅ ፡ ወጉ ፡ ግድ ፡ ቢለኝ
አባትዬ ፡ እልሃለሁ
ድረስልኝ ፡ ጠፍቻለሁ

ክብር ፡ ጠፍቶ ፡ ቅጥር ፡ ፈርሶ
ጠላት ፡ ገባ ፡ ወደቤቴ
ሰላም ፡ ቀርቶ ፡ ለቅሶ ፡ ሞልቶ
ዐይኔን ፡ በዕምባ

እንዳልርቅህ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ
የልጅ ፡ ወጉ ፡ ግድ ፡ ቢለኝ
አባብዬ ፡ እልሃለሁ
ድረስልኝ ፡ ጠፍቻለሁ

አዝ፦ መንፈስህን ፡ አትውሰድብኝ
አብሮነትህ ፡ ከእኔ ፡ አይለይ ፡ እኔ???
መገኘትህ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ሰላሜ
ሃብቴ ፡ ቅርሴ ፡ እስከዘለዓለሜ

ያለአንተማ ፡ አቅም ፡ የለኝ ፡ እኔ
እግዚአብሔር ፡ ሃይሌ ፡ ነህ ፡ መድህኔ
ያለአንተማ ፡ ጉልበት ፡ የለኝ ፡ እኔ
እግዚአብሔር ፡ ሃይሌ ፡ ነህ ፡ መድህኔ

ብዙ ፡ ጊዜ ፡ አሳዘንኩህ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ (፪x)
ብዙ ፡ ጊዜ ፡ በደል ፡ ሰራሁ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ
ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ
ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ራርተህ
ዛሬም ፡ ቆሜ ፡ ዘምራለሁ
ስላቀፍከኝ ፡ በፍቅርህ (፪x)