From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ መራመድ ፡ ሲያቅተኝ ፡ በጽድቅ ፡ ጐዳና
ነፍሴም ፡ ስትጨነቅ ፡ በኀጢአት ፡ ፈተና
ሥጋዬም ፡ ሲረክስ ፡ ጠፍቶ ፡ ህሊናዬ
እንደሰው ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ
ጨክኖ ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ
መጠቋቆሚያ ፡ ሲያደርገኝ ፡ ሰው ፡ ሁሉ
እንግዲህ ፡ ተስፋም ፡ የለው ፡ እያሉ
መች ፡ ቀረሁ ፡ ወድቄ ፡ ተሸማቅቄ
ከአምላኬ ፡ ጉያ ፡ እንዲያው ፡ ርቄ
እንደገና ፡ አረገኝ ፡ ቀና
እንደገና ፡ አረገኝ ፡ ቀና (፪x)
አዝ፦ መራመድ ፡ ሲያቅተኝ ፡ በጽድቅ ፡ ጐዳና
ነፍሴም ፡ ስትጨነቅ ፡ በኀጢአት ፡ ፈተና
ሥጋዬም ፡ ሲረክስ ፡ ጠፍቶ ፡ ህሊናዬ
እንደሰው ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ
ጨክኖ ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ
ምህረትህን ፡ የለመደ ፡ አመለኛ
ተው ፡ ቢሉን ፡ የማይሰማ ፡ እልከኛ
ብለው ፡ ፈረዱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፍቅር
በቸርነቱ ፡ ብዙ ፡ የተረዱ
የራሳቸውን ፡ ምሶሶ ፡ ትተው
የሰውን ፡ ጉድፍ ፡ የሚያዩ ፡ አጥርተው (፪x)
አዝ፦ መራመድ ፡ ሲያቅተኝ ፡ በጽድቅ ፡ ጐዳና
ነፍሴም ፡ ስትጨነቅ ፡ በኀጢአት ፡ ፈተና
ሥጋዬም ፡ ሲረክስ ፡ ጠፍቶ ፡ ህሊናዬ
እንደሰው ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ
ጨክኖ ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ
ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የማልጨርሰው
ውለታ ፡ አለብኝ (፪x) ፡ ብዙ ፡ የማላውቀው
ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የማልጨርሰው
ውለታ ፡ አለብኝ (፪x) ፡ ብዙ ፡ የማላውቀው
|