አትተወኝ (Atetewegn) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 1.jpeg


(1)

አያምረኝም
(Ayamregnm)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

 
አንዳንዴ ፡ ሲከፋኝ ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ መሄጃው ፡ ሲጠፋኝ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ እጮሃለሁ ፡ ፊትህን ፡ እፈልጋለው
ዝም ፡ አትበለኝ ፡ አትተወኝ ፡ ረዳቴ
የህመሜ ፡ ፈዋሽ ፡ አንተው ፡ ነህና ፡ መድሃኒቴ
(፪x)

ምድረ ፡ በዳው ፡ ሲያንገላታኝ ፡ ሃሩሩ ፡ ሲያደክመኝ
አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚቆም ፡ ከጐኔ
እምባዬን ፡ አፍስሼ ፡ ተማጸንኩህ ፡ ያኔ
አንተም ፡ ደረስክልኝ ፡ አልጨከንክም ፡ በእኔ

"በመከራዬ ፡ ሰዓት ፡ የረዳኽኝ ፣ በጭንቄ ፡ ሰዓት ፡ የደረስክልኝ
ዛሬም ፡ አልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አባክህን"

አዝ፦ አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ማንነቴን
አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ እኔነቴን
አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ደካማነቴን
አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ውስጤን ፡ ጓዳዬን

አንዳንዴ ፡ ሲከፋኝ ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ መሄጃው ፡ ሲጠፋኝ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ እጮሃለሁ ፡ ፊትህን ፡ እፈልጋለው
ዝም ፡ አትበለኝ ፡ አትተወኝ ፡ ረዳቴ (ረዳቴ)
የህመሜ ፡ ፈዋሽ ፡ አንተው ፡ ነህና ፡ መድሃኒቴ (ዝም ፡ አትበለኝ)
(፪x)

ከአንተ ፡ ወዴት ፡ የት ፡ እሄዳለሁ ፡ ሚስጥረኛዬ ፡ ነህ
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ የምትቀርበኝ ፡ ጓዴ
ዛሬስ ፡ መላው ፡ ጠፋኝ ፡ መግቢያው ፡ መውጪያው ፡ ሁሉ
ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ልሁን ፡ እንደቃልህ

"ያኔ ፡ በልጅነቴ ፡ ወራት ፣ ድምጽህን ፡ ለመስማት ፡ የነበረኝ ፡ ጉጉትና ፡ ናፍቆት
ዛሬ ፡ ግን ፡ ከውስጤ ፡ ጠፋና ፡ ወደአንተ ፡ እጮሃለሁ ፡ እባክህን (፪x)"

አዝ፦ አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ማንነቴን
አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ እኔነቴን
አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ደካማነቴን
አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ውስጤን ፡ ጓዳዬን