አስታውሳለው (Astawesalew) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 1.jpeg


(1)

አያምረኝም
(Ayamregnm)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

አስተምረኝ ፡ ጌታዪ ፡ ሆይ ፡ አስተካክላት ፡ ሕይወቴን
መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ስራመድ ፡ አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሁን (፪x)

ክፉና ፡ ደጉን ፡ ለይቶ ፡ ሳያውቀው
አስተምረኝ ፡ አለ ፡ ሌላው ፡ እንዳይነካው
እንካ ፡ ተረከባት ፡ ሕይወቴን ፡ አደራ
በቤትህ ፡ አንድኖር ፡ አንተን ፡ እንድፈራ

ልጅነቴን/ጉብዝናዬን ፡ ንገሥበት
እስከ ፡ እርጅና ፡ እስከ ፡ ሽበት
ክበርብኝ ፡ ለየኝና
ታናሹን ፡ የአንተን ፡ ብላቴና (፪x)

መልካም ፡ አባት ፡ መቼ ፡ ይጥላል(፪x)
ቃልኪዳኑን ፡ ይጠብቃል (፪x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ አደራ ፡ ላለው ፡ በመንገዱ ፡ ለተከተለው
ያቆመዋል ፡ በቤቱ ፡ ተክሎ ፡ ያጸናዋል ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ ብሎ (፪x)

አስተምረኝ ፡ ጌታዪ ፡ ሆይ ፡ አስተካክላት ፡ ሕይወቴን
መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ስራመድ ፡ አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሁን (፪x)

(አስታውሳለው) ፡ ወንድሞቼን ፡ እህቶቼን ፡ የጨቅላነት ፡ ጓደኞቼን
(አስታውሳለው) ፡ ኧረ ፡ አይጠፋም ፡ ከአዕምሮዬ ፡ የልጅነት ፡ ትዝታዬ
(አስታውሳለው) ፡ ተሰብስበን ፡ ስንዘምር ፡ አንዱ ፡ ለአንዱ ፡ ያለው ፡ ፍቅር
(አስታውሳለው) ፡ ክፋት ፡ የለ ፡ መሀላችን ፡ ያ ፡ ቅን ፡ ዘመን ፡ አቤት ፡ ሲያምር