አንተ ፡ ባለአደራ (Ante Baleadera) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 1.jpeg


(1)

አያምረኝም
(Ayamregnm)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

 
"እንዲህም ፡ አላቸው። 'ወደ ፡ ዓለም ፡ ሁሉ ፡ ሂዱ። ወንጌልንም ፡ ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ስበኩ።'" የማርቆስ ፡ ወንጌል ም. ፲፮ : ቁ.፲፭

አዝ፦ አንተ ፡ ባለአደራ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
አንተ ፡ መልዕክተኛ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
ተነስ ፡ መጽሓፉን ፡ አንሳ ፤ ተነስ ፡ ሚስጥሩን ፡ ግለጠው
ተነስ ፡ ግራ ፡ ለተጋባው ፤ ተነስ ፡ ልቡን ፡ አሳርፈው
(፪x)

የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኝ ፡ እያሉ
በጓዳቸው ፡ ሆነው ፡ ስንቶች ፡ ያለቅሳሉ ፡ አሄ
አንተ ፡ በዳንክበት ፡ መዳን ፡ አስባቸው
የእውነትን ፡ ቃል ፡ ይዘህ ፡ ሂድ ፡ ድረስላቸው ፡ እህ ፡ ሂድ ፡ ድረስላቸው

ብድራትህን ፡ ትኩር ፡ ብለህ ፡ ተመልከትና
የቀድሞው ፡ ነገር ፡ ትውስ ፡ ይበልህ ፡ እስኪ ፡ እንደገና
ያኔ ፡ የነበረው ፡ ትኩስ ፡ ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ቢቀና
ያቀናልሃል ፡ አምላክህ ፡ ደግሞ ፡ የአንተን ፡ ጐዳና

አዝ፦ አንተ ፡ ባለአደራ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
አንተ ፡ መልዕክተኛ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
ተነስ ፡ መጽሓፉን ፡ አንሳ ፤ ተነስ ፡ ሚስጥሩን ፡ ግለጠው
ተነስ ፡ ግራ ፡ ለተጋባው ፤ ተነስ ፡ ልቡን ፡ አሳርፈው
(፪x)

በሚብለጨለጨው ፡ ውበቷ ፡ ተማርከው
ስንቶች ፡ ሲኦል ፡ ገቡ ፡ ከምድር ፡ ተስማምተው ፡ አሄ
የሰማዩን ፡ ክብር ፡ የላዩን ፡ ሳያውቁ
መቃብር ፡ ወረዱ ፡ ሃያላን ፡ አለቁ ፡ እህህ ፡ ጠቢባን ፡ አለቁ

ወንጌሉን ፡ ይዘህ ፡ ሳትመሰክር ፡ ዘመን ፡ አለፈህ
ሰዉ ፡ እንደቅጠል ፡ በቀን ፡ በማታ ፡ እየረገፈ
መክሊቱን ፡ ቀብረህ ፡ ሳታተርፍበት ፡ ጌታ ፡ እንዳይመጣ
የተሰጠህን ፡ አደራ ፡ ይዘህ ፡ ፈጥነህ ፡ በል ፡ ውጣ ፡ አሄ

አዝ፦ አንተ ፡ ባለአደራ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
አንተ ፡ መልዕክተኛ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው
ተነስ ፡ መጽሓፉን ፡ አንሳ ፤ ተነስ ፡ ሚስጥሩን ፡ ግለጠው
ተነስ ፡ ግራ ፡ ለተጋባው ፤ ተነስ ፡ ልቡን ፡ አሳርፈው
(፪x)