ተስፋ ፡ አድርጌ (Tesfa Adregie) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 7.jpg


(7)

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
(Zarie Lay Qomie Negen Ayalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

ክብሬ ፡ ጌጤ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሽልማቴ
አጠገቤ ፡ ሳይህ ፡ ወደድኩህ ፡ አባቴ
ደጅ ፡ አላስጠናኸኝ ፡ አንተን ፡ ለማግኘት
ሳልፈልግህ ፡ መጥተህ ፡ ገባህ ፡ ከእኔ ፡ ቤት

አዝ፦ አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ
ጌታን ፡ ተማምኜ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፪x)

ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፬x)

የጠበኩት ፡ ሁሉ ፡ ያሰብኩት ፡ ባይሞላ
አንተ ፡ ካለህልኝ ፡ ምነው ፡ ባይበላ
ተስፋዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሙጥኝ ፡ እላለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ኖሮ ፡ ሞት ፡ ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነው

ትምክቴ ፡ ነህ ፡ በአንተ ፡ እታመናለሁ
የትናንቱን ፡ እንዴት ፡ ረሳዋለሁ
ተንከባክበህ ፡ አሳድገኸኛል
ለነገዬ ፡ ምንስ ፡ ያስፈራኛል (፪x)

ዓለም ፡ ሁሉ ፡ ክዶህ ፡ ብቻዬን ፡ ብቀር
እኔስ ፡ አለኝ ፡ ለእኔ ፡ ሕያው ፡ ምስክር
የልጅነቴ ፡ አምላክ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆነሃል
ጐጆዬ ፡ ስትገባ ፡ ሙሉ ፡ ዓይኔ ፡ አይቶሃል

አዝ፦ አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ
ጌታን ፡ ተማምኜ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፪x)

ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፬x)

የአጀበ ፡ ሲበተን ፡ ጐኔ ፡ የነበረው
ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ ወረት ፡ ሲቀይረው
አንዱ ፡ እንደ ፡ ሺህ ፡ ሆነ ፡ ቤቴን ፡ አድምቀሃል
የጐደለኝ ፡ የለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆነሃል