የሞት ፡ አዋጅ (Yemot Awaj) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

Yemot Awaj
(Yemot Awaj)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

አይሆንም በሕይወቴ
ጋልብጦታል ኢዬሱስ አባቴ

የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አምበሳ
ዙሪያ ዙሪያዬን ሲያዣብብ ሰላሜን ደርሶ ሊነሳ
መጣ ከሰማይ ወረደ ነደደ ያአምላኬ ቁጣ
በሳት ቅጥሩ ቀጠረኝ ጠላት በበቀል ሳይወጣ

ስልጣን የለውም በኔ ላይ
አለቃ አይሆንም የበላይ
እንዲያው አይደለም መጓደዴ
በመስቀል ሞት መወለዴ

የስንቱን ጀግና ቤት ደፍሮ መቅሰፍቱን ይዞ ሲገባ
አሳየኝ ገና ከሩቁ አጥፊውን ገዳዩን ሌባ
ሸንጎ ሰብስቦ ሲመክር ታሪኬን መና ሊያደርገው
ምልክት ሰጦ አስመለጠኝ እኔ ማመልከው እንዲህ ነው

ስልጣን የለውም በኔ ላይ
አለቃ አይሆንም የበላይ
እንዲያው አይደለም መጓደዴ
በመስቀል ሞት መወለዴ