ነገን ፡ አያለሁ (Negen Ayalehu) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 7.jpg


(7)

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
(Zarie Lay Qomie Negen Ayalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሰላም ፡ ያገኘሁት
ጻዲቁን ፡ ሳምን ፡ ነው ፡ የተረጋጋሁት
የቀድሞ ፡ ታሪኬ ፡ እንደዚህ ፡ አልነበረም
በናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ሕይወቴ ፡ አማረ

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ሆኜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
ተስፋን ፡ የሰጠኝ ፡ የታመነ ፡ ነው
አላሻግርም ፡ ብሎ ፡ ያስቸገረ
በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ተሰብሮ ፡ ታየ

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ወዳጄ ፡ የዘለዓለም ፡ ወዳጄ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ሰላሜ ፡ የዘለዓለም ፡ ሰላሜ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ እረፍቴ ፡ የዘለዓለም ፡ እረፍቴ (፫x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ወዳጄ ፡ የዘለዓለም ፡ ወዳጄ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ሰላሜ ፡ የዘለዓለም ፡ ሰላሜ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ እረፍቴ ፡ የዘለዓለም ፡ እረፍቴ (፫x)

(ሰላሜ ፡ እረፍቴ ፡ ወዳጄ ፡ የዘለዓለም ፡ ወዳጄ)

ዘመድ ፡ አልባ ፡ ሕይወት ፡ በኢየሱስ ፡ ሲተካ
አስገራሚ ፡ ውህደት ፡ ሰላም ፡ አለው ፡ ለካ
በተስፋ ፡ ያማረ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
በለመለመው ፡ መስክ ፡ መኖር ፡ ጀምሪያለሁ

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ሆኜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
ተስፋን ፡ የሰጠኝ ፡ የታመነ ፡ ነው
አላሻግርም ፡ ብሎ ፡ ያስቸገረ
በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ተሰብሮ ፡ ታየ

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ወዳጄ ፡ የዘለዓለም ፡ ወዳጄ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ሰላሜ ፡ የዘለዓለም ፡ ሰላሜ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ እረፍቴ ፡ የዘለዓለም ፡ እረፍቴ (፫x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ወዳጄ ፡ የዘለዓለም ፡ ወዳጄ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ሰላሜ ፡ የዘለዓለም ፡ ሰላሜ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ እረፍቴ ፡ የዘለዓለም ፡ እረፍቴ (፫x)