ኃጢአት ፡ ተሰረየ (Hateyat Tesereye) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 7.jpg


(7)

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
(Zarie Lay Qomie Negen Ayalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

ኢየሱስ ፡ ስለእኛ ፡ መስቀል ፡ ተሸክሞ
ቀራንዮ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ በጅራፍ ፡ ተገርፎ
ጐልጐታ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ በግፍ ፡ ተሰቀለ
እንደጅራት ፡ ደሙ ፡ በሜዳ ፡ ፈሰሰ

ሞተ ፡ ተቀበረ ፡ ተስፋ ፡ የለው ፡ ብለው
ተከታይ ፡ ልጆቹ ፡ በሃዘን ፡ ተመተው
አዳኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ በክብር ፡ ተነሳ
ከሙታን ፡ አለት ፡ ውስጥ ፡ እኛንም ፡ አስነሳን

በትንሳኤው ፡ ኃይል ፡ ማሸነፍ ፡ ያገኙ
ከሞት ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ የተሸጋገሩ
የከበረ ፡ ሠማይ ፡ ይጠብቃቸዋል
መኖሪያቸው ፡ ሁሌ ፡ በእዚያ ፡ ይሆናል

ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በጌታችን ፡ ደም
በደል ፡ ተሰረየ ፡ በመሲሁ ፡ ደም
የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አይታሰብም
ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድሃኒዓለም
የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አያገኘንም
ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድኃኒዓለም

ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በመሲሁ ፡ ደም
በደል ፡ ተሰረየ ፡ በጌታችን ፡ ደም
የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አይታሰብም
ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድሃኒዓለም (፪x)

አማኑኤል ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፬x)
መዳናችን ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)
አማኑኤል ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፬x)
መዳናችን ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)