ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ (Eyesus Bietie Geba) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 7.jpg


(7)

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
(Zarie Lay Qomie Negen Ayalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

እኔን ፡ የሚገርመኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የፍቅሩ ፡ ብዛት ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x)

የከበረ ፡ ነገር ፡ ከእርሱ ፡ ይፈልቃል
ተስፋ ፡ ያጣውን ፡ ሰው ፡ ሞገስ ፡ ያገኘዋል
ምስኪን ፡ ምጻተኛ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ አቅም ፡ ያነሰዉ
የኢየሱስ ፡ ደግነት ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ሰላም ፡ ወረሰዉ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ (፪x)
አባ ፡ ቤቴ ፡ ገባ
ነገሬን ፡ ቀየረው ፡ ቀያየረው
ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ ኦ ፡ ባረከው (፪x)

ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ (፪x)
አባ ፡ ቤቴ ፡ ገባ
ሕይወቴን ፡ ለወጠው ፡ ለዋወጠው
ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ ኦ ፡ ባረከው (፪x)

ህመሜን ፡ ከላዬ ፡ በፍቅሩ ፡ አከመው
የደከመ ፡ ሕይወቴን ፡ በቃሉ ፡ ፈወሰው
ፈጥኖ ፡ ተመለሰ ፡ የነፍሴ ፡ እርካታ/ደስታ
እስኪ ፡ ለጌታዬ ፡ ልቅረብ/አምጡልኝ ፡ በምሥጋና (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ (፪x)
አባ ፡ ቤቴ ፡ ገባ
ነገሬን ፡ ቀየረው ፡ ቀያየረው
ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ ኦ ፡ ባረከው (፪x)

ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ (፪x)
አባ ፡ ቤቴ ፡ ገባ
ሕይወቴን ፡ ለወጠው ፡ ለዋወጠው
ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ ኦ ፡ ባረከው (፪x)

ዓይኖቼ ፡ ሲቀኑ ፡ ጌታ ፡ ወዳለበት
ጠል ፡ ከላይ ፡ ወረደ ፡ አባቴ ፡ ካለበት
በትዝታ ፡ መኖር ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ጠፋ ፡ ከሕይወቴ
ፈጥኖ ፡ ሲሆንልኝ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ሠማይ ፡ እረዳቴ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ (፪x)
አባ ፡ ቤቴ ፡ ገባ
ነገሬን ፡ ቀየረው ፡ ቀያየረው
ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ ኦ ፡ ባረከው (፪x)

ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ (፪x)
አባ ፡ ቤቴ ፡ ገባ
ሕይወቴን ፡ ለወጠው ፡ ለዋወጠው
ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ ኦ ፡ ባረከው (፪x)

ብቻዬን ፡ ትቶኝ ፡ አልሄደም ፡ ጌታዬ ፣ ጌታዬ
ለብቻዬ ፡ ትቶኝ ፡ አልሄደም ፡ ወዳጄ ፣ ወዳጄ
ለአንድ ፡ አፍታ ፡ ትቶኝ ፡ አልሄደም ፡ ጌታዬ ፣ ጌታዬ
ብቻዬን ፡ ትቶኝ ፡ አልሄደም ፡ ወዳጄ ፣ ወዳጄ
(፪x)

ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ (፯x)
አንተ ፡ ብቻ ፡ . (1) .