አልረሳም (Alresam) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 7.jpg


(7)

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
(Zarie Lay Qomie Negen Ayalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

አልረሳም ፡ አልረሳም ፡ አልረሳም
ጌታ ፡ ውለታህን ፡ አልረሳም
ከአፈር ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ሲያነሳኝ
ለወግ ፡ ለማዕረግ ፡ ሲያበቃኝ
አልረሳም ፡ እኔስ ፡ አልረሳም

አልረሳም ፡ እኔስ ፡ አልረሳም (፬x)
ፍቅሩን ፡ አልረሳም ፡ ምህረቱን ፡ አልረሳም
ችሎታውን ፡ አልረሳም ፡ ያረገውን ፡ አልረሳም

ያባትነትህን ፡ ክብርህን ፡ አይቻለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ
ለነገ ፡ ሚያስፈራኝ ፡ ሚያሰጋኝ ፡ የለኝም
አምላኬ ፡ ዘለዓለም ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

አንተው ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
አባው ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ በልልኝ
አንተው ፡ ከፍ

እስኪ ፡ ማነው ፡ የደሃ ፡ አደጉ ፡ አባት
ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው ፡ ለምስኪኑ ፡ ደራሽ
ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው ፡ የመበለት ፡ ዳኛ
ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው ፡ ለተጠቃው ፡ ፈራጅ
እስኪ ፡ ማነው ፡ ከአምላኬ ፡ በቀር
እስኪ ፡ ማነው ፡ ከውዴ ፡ በቀር
ኧረ ፡ እስኪ ፡ ማነው ፡ ከኢየሱስ ፡ በቀር
እስኪ ፡ ማነው ፡ ከአባቴ ፡ በቀር
እስኪ ፡ ማነው ፡ ከአምላኬ ፡ በቀር
እስኪ ፡ ማነው ፡ ከውዴ ፡ በቀር
እስኪ ፡ ማነው ፡ ከኢየሱስ ፡ በቀር
እስኪ ፡ ማነው ፡ ከአባቴ ፡ በቀር

ለማን ፡ ተደረገ ፡ ለማንስ ፡ ሆነ
ለእኔ ፡ የሆንከውን ፡ እንዴት ፡ ልርሳው (፪x)
ለማን ፡ ተደረገ ፡ ለማንስ ፡ ሆነ
ለእኔ ፡ የሆንከውን ፡ እንዴት ፡ ልርሳው (፪x)

እስኪ ፡ ላምጣ ፡ ላቅርብ ፡ ሙሉ ፡ ክብር
አንተ ፡ እኮ ፡ ክብሬ ፡ ነህ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ልበል
ውርደቴን ፡ በክብር ፡ ለውጠህ ፡ አይቻለሁ
ከሰው ፡ የተለየ ፡ ምሥጋናን ፡ ይዣለሁ

እኔስ ፡ አልረሳም ፡ ፍቅሩን ፡ አልረሳም
እኔስ ፡ አልረሳም ፡ አልረሳም
እኔስ ፡ አልረሳም ፡ አልረሳውም
እኔስ ፡ አልረሳም ፡ ፍቅሩን ፡ አልረሳም
እኔስ ፡ አልረሳም ፡ ምህረቱን ፡ አልረሳም
እኔስ ፡ አልረሳም ፡ ችሎታውን ፡ አልረሳም