አልሻም (Alesham) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 7.jpg


(7)

ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ነገን ፡ አያለሁ
(Zarie Lay Qomie Negen Ayalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

በረሃብ ፡ ቀጠና ፡ አይደለሁም ፡ እኔ
ልምላሜ ፡ ረግፎ ፡ አልገደለኝ ፡ ጠኔ
በአረንጓዴው ፡ ገነት ፡ ምንጭ ፡ በሚፈልቅበት
እንድኖር ፡ ተፈርዷል ፡ በኢየሱስ ፡ ዳኝነት

አዝአልሻም ፡ ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም (፪x)
አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ)

ለምንድን ፡ ነው ፡ አሉኝ ፡ ክርስትያን ፡ የሆንከው
ሁልጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ምትለው
እስቲ ፡ ልንገራችሁ ፡ ይህንን ፡ ሚስጥር
. (2) . ፡ አይሎ ፡ ነው ፡ የመስቀሉ ፡ ፍቅር

አዝአልሻም ፡ ከአንተ/ከእርሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም (፪x)
አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ)

ነፍሴ ፡ አዋጅ ፡ ሰምታ ፡ የሞትን ፡ ቀጠሮ
ፍጥረት ፡ ሲያወራ ፡ የሽንፈት ፡ እሮሮ
ሕይወት ፡ ያበዛልኝ ፡ ማነው ፡ ከተባለ
አዳኙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በዙፋኑ ፡ ያለ

አዝአልሻም ፡ ከእርሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም (፪x)
አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ)

እስግዲህ ፡ በኢየሱስ ፡ ተደላድያለሁ
ዓለም ፡ የማይሰጠውን ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ
ታዲያ ፡ ለምን ፡ ልሩጥ ፡ ለምን ፡ ልቅበዝበዝ
እስቲ ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ እርፍ ፡ ልበል
እርፍ ፡ እርፍ ፡ እርፍ ፡ እርፍ ፡ ድግፍ
ጥግት ፡ ጥግት