ተዉኝማ (Tewugnema) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 5.jpg


(5)

ተዉኝማ
(Tewugnema)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)


ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ
(ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ)
እኮ ፡ ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ
(ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ)

ሁሉን ፡ ችሎ ፡ ዓይኔ ፡ ስላየ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ከሰው ፡ የተለየ
(ሁሉን ፡ ችሎ ፡ ዓይኔ ፡ ስላየ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ከሰው ፡ የተለየ)
ኢሄ ፡ ጌታ ፡ ከሰው ፡ ተለየ ፡ ኢሄ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሰው ፡ ተለየ (፪x)

አንገት ፡ ያስደፋኝ ፡ ያሳነሰኝ
ከወዲህ ፡ ወድያ ፡ ያንገላታኝ
ጌታ ፡ ስትመጣልኝ ፡ በመንገዴ ፡ ላይ
ሸሸኝ ፡ ጠላቴ ፡ አንተን ፡ ከሩቅ ፡ ሲያይ
በእውነት ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ እዘዝ ፡ በእኔ ፡ ላይ

አሆሆሆዬ ፡ እወይ ፡ ወዬ ፡ (አሆዬ)
የፂዮን ፡ ልጅ ፡ (አሆዬ)
ተራው ፡ የአንቺ ፡ ነው ፡ ተራመጂ ፡ እንጂ (፪x)

እኔ ፡ አላወራም ፡ ፊቴ ፡ ከቆመው ፡ ከተራራዬ
ጌታን ፡ ሳመልክ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ይላል ፡ ወርዶ ፡ ከላዬ (፪x)

ፊቴ ፡ የቆመውን ፡ ይህን ፡ ተራራ
ጌታ ፡ ስትመጣልኝ ፡ ሆነብኝ ፡ ተራ
ጌታ ፡ የጠራው ፡ ሰው ፡ ሆኖ ፡ ከልቡ
አያገኘውም ፡ መርዙ ፡ የእባቡ
እንባው ፡ አይሆንለት ፡ የእርሱ ፡ ቀለቡ

ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ
(ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ)
እኮ ፡ ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ
(ተዉኝማ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ጌታ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ)

ሁሉን ፡ ችሎ ፡ ዓይኔ ፡ ስላየ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ከሰው ፡ የተለየ
(ሁሉን ፡ ችሎ ፡ ዓይኔ ፡ ስላየ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ከሰው ፡ የተለየ)
ኢሄ ፡ ጌታ ፡ ከሰው ፡ ተለየ ፡ ኢሄ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሰው ፡ ተለየ (፪x)

የአንበሳው ፡ ልጅ ፡ ተራው ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ተራመድ ፡ እንጂ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ዘመኑ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ተራመድ ፡ እንጂ
የጀግናው ፡ ልጅ ፡ ተራው ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ተራመድ ፡ እንጂ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ዘመኑ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ተራመድ ፡ እንጂ

እስኪ ፡ ተነስ ፡ ተነስ ፡ ተነስ ፡ ተነስ ፡ ተነስ
ጌታ ፡ ያየልህን ፡ ውረስ ፡ ውረስ ፡ ውረስ (፪x)

የአንበሳው ፡ ልጅ ፡ ተራው ፡ የአንቺ ፡ ነው ፡ ተራመጂ ፡ እንጂ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ዘመኑ ፡ የአንቺ ፡ ነው ፡ ተራመጂ ፡ እንጂ
የጀግናው ፡ ልጅ ፡ ተራው ፡ የአንቺ ፡ ነው ፡ ተራመጂ ፡ እንጂ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ዘመኑ ፡ የአንቺ ፡ ነው ፡ ተራመጂ ፡ እንጂ

እስኪ ፡ ተነሽ ፡ ተነሽ ፡ ተነሽ ፡ ተነሽ ፡ ተነሽ
ጌታ ፡ ያየልህን ፡ ውረሽ ፡ ውረሽ ፡ ውረሽ (፪x)

አሆሆሆዬ ፡ እወይ ፡ ወዬ ፡ (አሆዬ)
የፂዮን ፡ ልጅ ፡ (አሆዬ)
ተራው ፡ የአንቺ ፡ ነው ፡ ተራመጂ ፡ እንጂ (፪x)

እኔ ፡ አላወራም ፡ ፊቴ ፡ ከቆመው ፡ ከተራራዬ
ጌታን ፡ ሳመልክ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ይላል ፡ ወርዶ ፡ ከላዬ (፪x)

ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ (፪x)
ስትነካኩኝ ፡ ኢኸው ፡ ባሰብኝ
እኮ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ ፡ ተዉኝ
ልሂድ ፡ ልሩጥ ፡ ባለ ፡ ራዕይ ፡ ነኝ
ተዉኝ!