ሃይለኛ (Haylegna) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 5.jpg


(5)

Tewugnema
(Tewugnema)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

ሃይለኛ/4
ሃይለኛ ነው ያንቺ ጌታ
ሃይለኛ ነው ያንተ ጌታ
ለማንም የማይረታ
ሃይለኛ ነው የኔ ጌታ
 ሃይለኛ ነው የኛ ጌታ
ለማንም የማይረታ

ለማንም የማይረታ በማንም የማይረታ/4

ማንም በማይደርሰው በችግሬ ላይ
እኔ አበቃ ስል አንተ አለው እያልከኝ
ኑሮዬን ያጣፈጥክ እድሜዬን የቀጠልክ
አንተ ምን ልትባል በእኔ አንደበት እንዲ ልበል

ገናና/8

እቅም ባጣሽ ግዜ ዙሪያሽም ጨልሞ
ማነው ያበረታሽ ባጠገብሽ ቆሞ
ጌታ አይደል ያንቺ መከታ
ሰላምሽ የህይወትሽ ደስታ
እርሱን ምን ልትይው በፊቱ እስቲ ወድቀሽ እንዲ በይው

ገናና/8

ሃይለኛ/4
ሃይለኛ ነው ያንቺ ጌታ
ሃይለኛ ነው ያንተ ጌታ
ለማንም የማይረታ
ሃይለኛ ነው የኔ ጌታ
 ሃይለኛ ነው የኛ ጌታ
ለማንም የማይረታ

ለማንም የማይረታ በማንም የማይረታ/4
ጌታ የማይረታ ጌታ ነው የማይረታ/4

እስቲ ቆም ብለህ አንዴ አስተውለው
ውርደትን በክብር የቀየረው ማነው
ጌታ እኮ ያንተ መከታ ስላንተ ሁሌ ሚዋጋ
እርሱን ምን ልትለው በፊቱ እስቲ ሰግደህ እንዲ በለው

ገናና/8

ሰይፉ በእጁ ነው ይቆራርጣል
መርሹም በእጁ ነው ፈጥኖ ያጠራል
ኧረ ይሄን ጌታ ማን ሊችለው
ሲሰራ ማነው ሚከለክለው
እርሱ እኮ ኤልሻዳይ ነው/4

የኔን ጌታ ማን ይመስለዋል
እየሱሴን ማን ይመስለዋል
ጌታ ማን ይመስለዋል/8