From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ውበትህ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል
ኢየሱሴ ፡ እንተን ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ሲተረክ ፡ ቢዋል
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል
እንዳባቴ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል (፬x)
ካጠገቤ ፡ ቆመህ ፡ አበርትተኛል
ከወዳጅም ፡ ወዳጅ ፡ ወዳጅ ፡ ወዳጅ ፡ ሆነኸኛል
መደገፍ ፡ አንተን ፡ ነው ፡ መታመን ፡ ባንተ ፡ እንጂ
ሁሉን ፡ እየረታህ ፡ ሆንክልኝ ፡ ሞገስ
ሆንክልኝ ፡ ሞገስ (፪x)
ሆንክልኝ ፡ ብቃት (፪x)
ውበትህ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል
ኢየሱሴ ፡ እንተን ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ሲተረክ ፡ ቢዋል
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል
እንዳባቴ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል (፬x)
ካቻምናን ፡ አለፍኩኝ ፡ ባንተ ፡ በመደገፍ
ዘንድሮን ፡ አልሰጋም ፡ ስለሆንከኝ ፡ ሞገስ
ደስታ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ ለቅሶ ፡ ለጠላቴ
ይሄንን ፡ ያረገው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ አባቴ
ከፍ ፡ ይበል ፡ አባቴ (፬x)
ውበትህ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል
ኢየሱሴ ፡ እንተን ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ሲተረክ ፡ ቢዋል
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል
እንዳባቴ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል (፬x)
ማንንስ ፡ እረስተህ ፡ ማን ፡ ጥለህ ፡ ታውቃለህ
ይልቁን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ታደርጋለህ
ደካማው ፡ በረታ ፡ ቆመ ፡ በእግሮቹ
ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ እያየ ፡ ጠላቱ
እያየ ፡ ጠላቱ (፬x)
ውበትህ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል
ኢየሱሴ ፡ እንተን ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ሲተረክ ፡ ቢዋል
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል
እንዳባቴ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል (፬x)
|