ልቤን ፡ ጣልኩ (Lebien Talkut) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 3.png


(3)

ተሻገር ፡ ያለው
(Teshager Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

 
ልቤን ፡ ጣልኩት ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አሁንማ
እኔስ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይጥለኝ ፡ የማይከዳ (፪x)

በቁጥር ፡ ተቆጥሮ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ አይባልም
አንተ ፡ ለኔ ፡ ያረግከው ፡ ሚዛን ፡ አይለካውም (፪x)
አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ ብዬ ፡ ሙሉ ፡ አፌ ፡ ቢያወራ
እኔስ ፡ ኮራሁብህ ፡ አምላክ ፡ የለኝ ፡ ሌላ (፪x )

አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ ብዬ ፡ (አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ ብዬ)
ሙሉ ፡ አፌ ፡ ቢያወራ ፡ (ቢያወራ ፡ ቢያወራ)
እኔስ ፡ ኮራሁብህ ፡ (ኮራሁ) ፡ አምላክ ፡ የለኝ ፡ ሌላ

አዝ፦ ልቤን ፡ ጣልኩት ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አሁንማ
እኔስ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይጥለኝ ፡ የማይከዳ (፪x)

ተደላድያለሁ ፡ በርሱ ፡ ተወድጄ
ዝማሬ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የሞላው ፡ በአፌ (፪x)
ከእንግዲህ ፡ ወዲያ ፡ ልቤ ፡ አይገባም ፡ ስጋት
ለሰው ፡ የሚያዝነው ፡ ሆኖልኛል ፡ አባት (፪x)

ከእንግዲህ ፡ ወዲያ ፡ (ከእንግዲህ ፡ ወዲያ)
ልቤ ፡ አይገባም ፡ ስጋት (አይገባም ፡ አይገባም)
ለሰው ፡ የሚያዝነው ፡ (ኦ) ፡ ሆኖልኛል ፡ አባት (፪x)

አዝ፦ ልቤን ፡ ጣልኩት ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አሁንማ
እኔስ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይጥለኝ ፡ የማይከዳ (፪x)