From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ታለፈ
ኢየሱስ ፡ እየቀደመ ፡ ወዳጄ ፡ እየቀደመ
ውድዬ ፡ እየቀደመ (፪x)
ስንቱን ፡ ተራራ ፡ ባንተ ፡ አለፍኩኝ
ስንቱን ፡ ሸለቆ ፡ ውሃ ፡ ሞላኸው
ጌታዬ ፡ ባንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆነልኝ
ክብር ፡ ምስጋና ፡ ላንተ ፡ ይድረስህ (፪x)
በሕይወቴ ፡ በኑሮዬ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባህ
ጣልቃ ፡ እየገባህ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባህ ፡ መንገዴን ፡ አቀና
ጣልቃ ፡ እየገባህ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)
በአምላኬ ፡ ክንዱ ፡ ላይ ፡ ተደግፌ
በርሱ ፡ ደግነት ፡ አምናን ፡ አልፌ
ዘንድሮን ፡ አየሁ ፡ ጌታን ፡ ታምኜ
ላከብረው ፡ መጣሁ ፡ ሁሉንም ፡ ትቼ (፪x)
በሕይወቴ ፡ በኑሮዬ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባህ
ጣልቃ ፡ እየገባህ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባህ ፡ መንገዴን ፡ አቀናህ
ጣልቃ ፡ እየገባህ ፡ መንገዴን ፡ አቀናህ (፪x)
ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ ፡ ነህ
ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ
ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ (፪x)
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ ክብሬ
ጌትዬ ፡ መታመኛዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ ክብሬ
ውድዬ ፡ መታመኛዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ ክብሬ
ኢየሱስ ፡ መታመኛዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ ክብሬ (፪x)
|