From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እልፍ ፡ እልፍ ፡ እያልኩኝ ፡ ልሂድ ፡ እንጂ
ይከፈታል ፡ በፊቴ ፡ ያ ፡ ደጅ (፪x)
ይከፈታል ፡ በፊቴ ፡ ያ ፡ ደጅ (፬x)
ተሰብሮ ፡ አየሁኝ ፡ የናሱ ፡ ደጅ
ልሂድ ፡ ልራመድ ፡ የለኝ ፡ ከልካይ
ገና ፡ እሄዳለሁ ፡ ጨለማውን ፡ ጥሼ
እሻገራለሁ ፡ ሁሉን ፡ ረትቼ
እልፍ ፡ እልፍ ፡ እያልኩኝ ፡ ልሂድ ፡ እንጂ
ይከፈታል ፡ በፊቴ ፡ ያ ፡ ደጅ (፪x)
ይከፈታል ፡ በፊቴ ፡ ያ ፡ ደጅ (፬x)
አልሸበር ፡ አልፈራው ፡ ያ ፡ ጠላቴን
ከቦት ፡ የለም ፡ እሳቱ ፡ ማደሪያዬን (፪x)
ከቦት የለም እሳቱ ማደሪያዬን (፬x)
እልፍ ፡ ብዬ ፡ ጉድጓድ ፡ ቆፈርኩኝ
የኋላውን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ ያዝኩኝ
እልፍ ፡ በማለት ፡ ሚገኘው ፡ ደስታ
ለኔስ ፡ ሆነልኝ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ጌታ
እልፍ ፡ እልፍ ፡ እያልኩኝ ፡ ልሂድ ፡ እንጂ
ይከፈታል ፡ በፊቴ ፡ ያ ፡ ደጅ (፪x)
ይከፈታል ፡ በፊቴ ፡ ያ ፡ ደጅ(፬x)
መሸ ፡ ነጋ ፡ አትልም ፡ አንተ ፡ ስትሰራ
ጨለማ ፡ አይዝህ ፡ እየሱስ ፡ የኔ ፡ ጀግና
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
የትንሳዔው ፡ ንጉስ ፡ የሱስ ፡ የኔ ፡ አለኝታ (፪x)
ክበር ፡ የኔ ፡ አለኝታ (፪x)
ለቆልኛል ፡ ከአርያም ፡ መንፈሱን
አፈሰሰው ፡ ጌታዬ ፡ ቅባቱን (፪x)
አፈሰሰው ጌታዬ ቅባቱን (፬x)
መሸ ፡ ነጋ ፡ አትልም ፡ አንተ ፡ ስትሰራ
ጨለማ ፡ አይዝህ ፡ እየሱስ ፡ የኔ ፡ ጀግና
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
የትንሳዔው ፡ ንጉስ ፡ የሱስ ፡ የኔ ፡ አለኝታ (፪x)
ክበር የኔ አለኝታ (የኔ አለኝታ)
ክበር የኔ አለኝታ (ኦ የኔ አለኝታ)
ክበር የኔ አለኝታ (ኢየሱስ የኔ ጌታ)
ክበር የኔ አለኝታ (ኦ የኔ አለኝታ)
ክበር የኔ አለኝታ (ኢየሱስ የኔ አለኝታ)
|