From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው
እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
ሰማያትን ፡ በሃይሉ ፡ ያጸና
በምክሩም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ እሱ ፡ ገናና
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ለዘላለም (፪x)
አዝ፦በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው
እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፫x)
እስረኛውን ፡ የፈታ ፡ ያከበረ
ምስኪኑን ፡ ሰው ፡ በከፍታ ፡ ላይ ፡ ያኖረ
የባርነትን ፡ በትር ፡ የሰበረው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
አዝ፦በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው
እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ በተቀደሰ ፡ መቅደሱ ፡ አለ
ጨለማውን ፡ የለየ ፡ ቀኑን ፡ ብርሃን ፡ ይሁን ፡ ያለ
ዙፋኑ ፡ በሰማይ ፡ ነው ፡ በሰማይ ፡ ነው ፡ ኦሃሃሃ
እንደ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው (ያለ ፡ ማነው) (፬x)
|