From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በሕይወቴ ፡ ዘመን (፰x)
አልተውከኝም ፡ ፈጽሞ ፡ አልረሳኸኝም (፪x)
ለአንድ ፡ አፍታ ፡ አልረሳኸኝም (፪x)
እጅ ፡ ጭነህ ፡ መርቀኸኛል ፡ ተባረክ ፡ ብለህ
ለጠላቴ ፡ መልስን ፡ ሰጠኸው ፡ አትንካው ፡ ብለህ
እልፍ ፡ ስል ፡ የበረከት ፡ ምንጭ ፡ ያጋጥመኛል
ገና ፡ ሳልደርስ ፡ ስራዬን ፡ ሰርተህ ፡ ጠብቀኸኛል
ጠብቀኸኛል (፬x)
አቤት ፡ ያንተስ ፡ ነገር ፡ ስንቱ ፡ ይነገር
አቤት ፡ ያንተስ ፡ ስራ ፡ ስንቱ ፡ ይወራ (፪x)
በሕይወቴ ፡ ዘመን (፰x)
አልተውከኝም ፡ ፈጽሞ ፡ አልረሳኸኝም (፪x)
ለአንድ ፡ አፍታ ፡ አልረሳኸኝም (፪x)
ስላለፈው ፡ ልቤ ፡ ሲነሳ ፡ ሊያመሰግንህ
በመንገዴ ፡ ፈጥረህ ፡ ጠበቅከኝ ፡ ሌላ ፡ ተዓምር
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እጁን ፡ ባፉ ፡ ላይ ፡ እስኪጭን ፡ ድረስ
በሩቅ ፡ በቅርብ ፡ ተዓምር ፡ ተባለ ፡ ሆነኸኝ ፡ ሞገስ
ሆነኸኝ ፡ ሞገስ (፬x)
አቤት ፡ ያንተስ ፡ ነገር ፡ ስንቱ ፡ ይነገር
አቤት ፡ ያንተስ ፡ ስራ ፡ ስንቱ ፡ ይወራ (፪x)
በሕይወቴ ፡ ዘመን (፰x)
አልተውከኝም ፡ ፈጽሞ ፡ አልረሳኸኝም (፪x)
ለአንድ ፡ አፍታ ፡ አልረሳኸኝም (፪x)
|