From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ማዕበሉን ፡ በስልጣን ፡ የሚገስጽልኝ
ዞር ፡ በል ፡ የሚልልኝ
አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ አባት ፡ አለኝ (፪x)
ረዳት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ረዳት ፡ አለኝ (፪x)
ከእናት ፡ ካባቴም ፡ በላይ ፡ ለኔ ፡ ራርተህ ፡ ስላየሁ (አሃሃ ፡ አሃ)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እላለሁ
ስደክም ፡ አበርትተህ ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባህ (አሃሃ ፡ አሃ)
ጽዋዬም ፡ ተረፈልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ
ጌታ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ ፡ ውዴ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ (፪x)
ሰው ፡ ቢጥል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያነሳል (ሰው ፡ ቢጥል)
ሰው ፡ ቢጥል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያነሳል
ከብሮ ፡ ያከብራል ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል
ሰው ፡ ቢጥል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያነሳል (ሰው ፡ ቢጥል) (፪x)
እንቅልፍ ፡ እንደያዘው ፡ እንደተኛ ፡ ሰው (፪x)
መስሎኝ ፡ ነበር ፡ እኔስ ፡ ግድ ፡ ማይለው (፪x)
ኧረ ፡ ይሄስ ፡ ሰው ፡ ሃይለኛ ፡ ነው ፡ ተነሳና ፡ ዞር ፡ በል አለው
ኧረ ፡ ይሄስ ፡ ሰው ፡ ሃይለኛ ፡ ነው ፡ ተነሳና ፡ ጸጥ ፡ በል ፡ አለው
አዝ፦ማዕበሉን ፡ በስልጣን ፡ የሚገስጽልኝ
ዞር ፡ በል ፡ የሚልልኝ
አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ አባት ፡ አለኝ (፪x)
ረዳት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ረዳት ፡ አለኝ (፪x)
የምስኪን ፡ ወዳጅ ፡ ሆነህ ፡ በጐጆዬ ፡ ውስጥ ፡ ገባህ (አሃሃ ፡ አሃ)
የዘመመው ፡ ቤቴ ፡ ይኸው ፡ ባንተ ፡ ቀና
ታዲያ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ለምን ፡ ላጉረምርም (አሃሃ ፡ አሃ)
በጐጆዬ ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ ኢየሱስ ፡ ይክበር ፡ ውድዬ ይክበር
ጌትዬ ፡ ይክበር ፡ ወድዬ ፡ ይክበር
አዝ፦ማዕበሉን ፡ በስልጣን ፡ የሚገስጽልኝ
ዞር ፡ በል ፡ የሚልልኝ
አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ አባት ፡ አለኝ (፪x)
ረዳት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ረዳት ፡ አለኝ (፪x)
|