ያስለቀሰኝ ፡ ለሊት ፡ ኣለፈ (Yeseleqeseng Lelit Alefe) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 4.jpg


(4)

Talefe Ya Zemen
(Talefe Ya Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

ያስለቀሰኝ ለሊት አለፈ በየሱሴ አለፈ/2
ያስተከዘኝ ለሊት አለፈ በየሱሴ አለፈ/2

ችግሬን መናድ እርሱ ልማዱ ነው
ለኔ ያቃተኝ ሁሉ ለሱ ቀላል ነው
ትላንት አልሆን ያለ ነገ ደሞ ይሆናል
የእግዚአብሔር አሰራር ይህንን ያደርጋል

ያደርጋል ያደርጋል የኔ አምላክ ያደርጋል
ያደርጋል ያደርጋል የኔ ጌታ ያደርጋል

ያስለቀሰኝ ለሊት አለፈ በየሱሴ አለፈ/2
ያስተከዘኝ ለሊት አለፈ በየሱሴ አለፈ/2

በቃ የኔ ነገር ተስፋም የለውም
እኔ ምላቸው ብዙ ነበሩ
ጌታ ግን መቼ እንደኔ ሆነና
ችግሬን ናደው ብቃ አለና

አለና አለና በቃ እኮ አለና/3
አለና ጌታ እኮ በቃ አለና

ደስታዬ/3 ልበልህ ደስታዬ
ኩራቴ/3 ልበልህ ኩራቴ