From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በጠላቴ ፡ መንደር ፡ በድል ፡ ላራመደኝ ፡ ኦሆ ፡ ላራመደኝ (፪x)
እኔስ ፡ የዚህ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ አለብኝ ፡ ኦሆ ፡ አለብኝ (፪x)
በክብር ፡ ላይ ፡ ክብር ፡ ክብርን ፡ ላለበሰኝ ፡ ኦሆ ፡ ላስታጠቀኝ (፪x)
ምነው ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ እኔስ ፡ በሆንኩለት ፡ ኦሆ ፡ በሆንኩለት (፬x)
ዘመኑ ፡ የድል ፡ ነው ፡ የመከናዎን
ከአምላኬ ፡ የሰማሁት ፡ በመንፈስ ፡ ያወኩት ፡ የተረዳሁት
ዘመኑ ፡ የድል ፡ ነው ፡ የመከናዎን
ዘመኑ ፡ የድል ፡ ነው ፡ የመከናዎን (፪x)
በጠራራ ፡ ጸሐይ ፡ ደመናም ፡ ሳይታይ ፡ ኦሆ ፡ ደመናም ፡ ሳይታይ (፪x)
ምንጭን ፡ አፈለቀ ፡ ጌታ ፡ ከዓለቱ ፡ ላይ ፡ ኦሆ ፡ ጌታ ፡ ከዓለቱ ፡ ላይ (፪x)
እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ ከዓለቱ ፡ ጠጥቼ ፡ ኦሆ ፡ ከዓለቱ ፡ ጠጥቼ (፪x)
ዘመኑ ፡ የድል ፡ ነው ፡ እላለሁኝ ፡ ዛሬ ፡ ኦሆ ፡ እላለሁኝ ፡ ዛሬ (፬x)
ተረጋጋሁ ፡ መንፈሱ ፡ ሲነካኝ ፡ ተረጋጋሁ
ተረጋጋሁ ፡ ቅባቱ ፡ ሲነካኝ ፡ ተረጋጋሁ
አመለጥኩኝ ፡ ወዳጄን ፡ ሰምቼው ፡ አመለጥኩኝ
አመለጥኩኝ ፡ ጌታዬን ፡ ሰምቼው ፡ አመለጥኩኝ (፪x)
|