ሰዎች ፡ የዘጉት ፡ በር (Sewoch Yezegut Ber) - መስፍን ፡ ጉቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu 4.jpg


(4)

Talefe Ya Zemen
(Talefe Ya Zemen)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

ሰዎች የዘጉት በር አለቆች የያዙት
ስልጣናን ዙፋናን ሁሉ የተስማሙበት
ምንም ይሁን ምንም

እርሱ ሲመጣ አውቆ ይከፈታል
ጌታ ሲመጣ አውቆ ይከፈታል
ትልቁ እግዚአብሔር ይህንን ያደርጋል

ብዙ ሃያላኖች በምድር ላይ ነበሩ
አንዳቸውም ግን አሁን የሉም
ስራውና ስሙ አንድ የሆነው ጌታ
ይኸው አለ ገና ይኖራል እንደረታ
እርሱ ብቻ ገናና

አንተ ብቻ ገናና/2

ሰዎች የዘጉት በር …
እርሱ ሲመጣ …

ጠላት ይዝጋው ማንም ይዝጋው አልከፈት ያለው በር
ይኸው ተከፈት በፍጥነት
በተከፈተው በር ወጥቼ ይኸው ገናሁኝ
የጠላቴን ሰፈር አሸበርኩኝ
ጠላቴን ረገጥኩኝ/3

ሰዎች የዘጉት በር …
እርሱ ሲመጣ …

ብዙ ጉድጏዶችን ደጋግሜ ቆፍሬ ነበር
የፍልስጤም ሰዎች ደፈኑብኝ
እኔም ሳልሰለች ደጋግሜ ቆፈርኩኝ
ይኸው በምድር ሰፋው ሮሆቦት ሆንኩኝ/3
ሮሆቦት ሆንኩኝ በምድር በዛሁኝ

ሰዎች የዘጉት በር …
እርሱ ሲመጣ …